አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላላቅ የዱባይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ። የኢትዮጵያ መንግሥትም ባለሀብቶቹን እንደሚደግፍና እንደሚያበረታታቸው አረጋግጦላቸዋል።የዱባይ የንግድና የኢንዱስትሪ ምክር ቤት 18 ታላላቅ የዱባይ ኩባንያ መሪዎችን ያካተተ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደተገለጸው፤ የዱባይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት፣ በግንባታና በግንባታ መሣሪያዎች ማምረት እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግና በቱሪዝም መስኮች ለመሠማራት ተዘጋጅተዋል። የቢዝነስ ልዑካን ቡድኑን የመሩት የዱባይ የንግድና የኢንዱስትሪ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሚስተር አብዱል ራህማን ሰይፍ አል ገህሬር በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ የዱባይንና የኢትዮጵያን የቢዝነስ ግንኙነት ለማጠናከር ካለው ፍላጎትም በላይ ተግባራዊ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ለማሳያነትም በዱባይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለንግዱ ማኅበረሰቡ ከማሳየቱም በላይ በአገሪቱ ኢንቨስት በማድረግ የሚፈለጉትም ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸውና ከመንግሥት ጋር እንዲወያዩ ይህንኑ የልዑካን ቡድን ጉብኝትና ምክክር ማሰናዳቱን ገልጸዋል።
አብራችሁን በመጓዝ ለስኬት ላበቃችሁን ደንበኞቻችን በሙሉ እናመሰግናለን።
አፍሪካ አዲስ የተስፋ አህጉር እየሆነች ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ
በዓለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካ ተደማጭነትና መልካም ገጽታ እያደገ ነው
የአፍሪካ ህብረት መሪዎች የዛፍ ችግኝ ተከላ ሲያካሂዱ
የአፍሪካ ህብረት 18ኛው የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ
ህንፃውን የገነባችው ቻይና በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታትም ለህብረቱ የ100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች
Monday, January 02, 2012.
Monday, December 26, 2011
Monday, December 05, 2011.
Wednesday, May 16, 2012.
Wednesday,May 16,2012.
Saturday, May 12, 2012.
Monday, May 14, 2012.
Monday , May 07, 2012.
Sunday, May 13, 2012.
Sunday, May 06, 2012.
Saturday, May 05, 2012.
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢ እቃዎች ከጂቡቲ ወደብ ወደ ሃገር ቤት መግባት በሚገባቸው ጊዜ ባለመግባታቸው ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ እየተዳረግን ነው ሲሉ አንዳንድ አስመጪዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ተናገሩ።
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመረው የመንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም በተቀመጠለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የተጠናከረ የሕብረተሰብ ንቅናቄ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ አሳሰቡ፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የስነ ልክ ትምህርት በአስራ ስድስት ዩንቨርሲቲዎች መሰጠት መጀመሩን የብሔራዊ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ የዉጪ ባላሃብቶች በኮምቦልቻ አዳዲስ ፋብሪካዎችን እየገነቡ ነው።
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የ11 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር የእርዳታ ስምምነት ዛሬ ተፈራረሙ፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በካይሮ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሶስተኛ ወገን መድህን ሽፋን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ከ280 ሺ በላይ ተሽከርካሪዎች መመዝገባቸውን የሶስተኛ ወገን መድህን ፈንድ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም የቴሌኮሚዩኒኬሽንና የመረጃ ማህበረሰብ ቀን ዛሬ ይከበራል፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት የውጭ ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ጠየቁ።
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃ መገኛ ከሆኑት የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውሃዎች የሚመነጨውን የፍሎራይድ ኬሚካል መጠንን ለመቀነስ እየሰራ ነው።
Friday May 11 , 2012
Friday , May 04 , 2012
Friday , April 27 , 2012
Wednesday, October 19, 2011.
Wednesday, October 12, 2011
Sunday, April 29, 2012.