ስለ ፋና (1)

 ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ

ጣቢያችን በ 1987 ዓ ም ሲቋቋም በኃላ ቀር መሳሪያዎችና በጥቂት የሰው ሃይል በሀገራችን የብሮድካስት ሚድያ አዲስ አቀራረብ ይዞ ወደ ስራ ገባ። በሂደትም አደረጃጀቱንና የፕሮግራም ይዘቱን እያሻሻለና ችግሮቹን እየቀረፈ ገስጋሴዉን ቀጠለ። ህብረተሰብ ተኮር ፕሮግራሞች ላይ በማጠንጠን የሚታወቀውና ለህዝባችን ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ኑሮ መሻሻልና መዳበር የሚተጋው ጣቢያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማጮቹንና ተባባሪቹን ያበረከተ ከፍተኛ ተደማጭ ሚድያ የሆነ መጣ።

ተቋማችን ራሱን በተማረ የሰዉ ሃይል ያሟላና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ያዋሃደ የማስተማር፣ የማሳወቅና የማዝናናት ሚናዉን አጠናክሮ በመቀጠል በሀገራችን ሚዲያ ለውጥ ማምጣቱን ቀጠለ።  ከአዲሰ አበባ ዉጪ በ 11በብሮድካስቲንግ ሚዲያ ልዩነት በመፍጠር በሀገራችን የሚድያ ታሪክ በሚያስገርም ፍጥነት ከአዲስ አበባ ውጪ በ11 የክልል ከተሞች የኤፍ̣.ኤም ጣቢያችን የተሟላና በተደራጀ የሰው ሃይልና የሬድዮ ቴክኖሎጂ በማሟላት እርስ በራስ በማስተሳሰር ለመክፈት ቻለ። በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ 12 የኤፍ̣.ኤም ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

በሀገራችን ታሪክ ለሚደያ ተብሎ የተሰራ ባለ 11 ፎቅ የሚድያ ኮምፕሌክስ ህንፃ ባለቤት የሆነው ተቋማችን በአሁኑ ሰዓት ከሀገራችን አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የሚድያ ተቋም የመሆን ህልሙን ለማሳካት ከጥር 2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አድጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ኤፍ̣.ኤም ጣቢያዎቹን ወደ 20 ለማሳደግና የቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር እየሰራ ነው።

ለዚህ ሁሉ ስኬት የአድማጮቻችንና የተባባሪዎቻችን ሚና ከፍተኛ መሆኑን የሚያምነው ጣቢያችን በአሁኑ ሰዓት በማዕከል 360 እና በክልል 304 በድምሩ 664 ጠንካራ የባለቤትነት መንፈስና የህዝብ ወገንተኝነት ያላቸው ሰራተኞች አሉት።

በሳምንት የ38 ሀገር አቀፍ ስርጭት በማቅረብ ጀምሮ ዛሬ በሀገር አቀፍና በሁሉም የኤፍ̣.ኤም ጣቢያዎቹ በእያንዳንዳቸው በቀን 18 ሰዓት ያሰራጫል።:

ራዕይ:

በኢትዮጵያና በአፍሪካ ተመራጭ ፣ ተደራሽና ቀዳሚ የንግድ ሚድያ መሆን፣

ተልዕኮ:

ጥራትና ብቃት ባለው ሚድያ አገልግሎት የበለፀገችና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት የለውጥ ሃሳቦችን በማራመድ ተመራጭና ትርፋማ የንግድ ሚድያ ሆኖ ማገልገል ነዉ።