ጎግል ቤተሰብ የልጆቹን አንድሮይድ ስልክ ከሩቅ ሆኖ የሚቆጣጠርበት መተግበሪያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሁኑ ትውልድ ከቴክኖሎጂ ጋር ያለው ትስስር ከእለት እለት እየጨመረ መጥቷል።

ከዚህ የተነሳም ወላጆች ልጆቻቸው ወዳልተፈለገ ነገር እንዳይገቡ ስጋታቸው እየጨመረ መምጣቱ በስፋት ይስተዋላል።

ሆኖም ግን ልጆችን ከቴክኖሎጂ መነጠል አስቸጋሪ ሆኗል፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በአሁኑ ጊዜ ልጆች የሚማሩትን ትምህርት ለማጥናትም ይሆን ለመዝናናት ቴክኖሎጂን እንደ አማራጭ እየተጠቀሙ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው።

ስለዚህ ያለው ብቸኛ አማራጭ ልጆች የሚፈልጉትን የቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ከሰጠናቸው በኋላ አጠቃቀማቸውን መገደብ ነው።

ለዚህ ገድሞ ጎግል አዲስ ያቀረበው መተግበሪያ የልጆቻችንን አንድሮይድ ስማርት ስልኮች ከሩቅ ሆነን ለመቆጣጣር ስለሚያስችል በመሆኑ ጠቃሚ ነው ተብሏል።

መተግበሪያው “ፋሚሊ ሊንክ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ ቤተሰቦች ልጆቻቸው በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ላይ የሚያደርጉትን ነገር ከሩቅ ሆነው ለመቆጣጣር ያስችላል።

ልጆች ከጎግል ፕሌይ ላይ ምን አይነት መተግበሪያዎችን እያወረዱ (ዳወንሎድ) እያደረጉ እንደሆነ ከሩቅ ለመከታተል እና መተግበሪያው የማይጠቅማቸው ከሆነ ለማስቆም ያስችላል።

Families_2.png

እንዲሁም በኢንተርኔት ከሚያገኟቸው ጓደኞቻቸው ጋር ምን ያክል ጊዜ እንደሚያሳልፉ ለማየት፣ በኢንተርኔት ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ለመገደብ እና በወር እና በሳምንት ምን ያክል ጊዜ እንተርኔት ላይ እንዳሳለፉ ለመቆጣጣር ያስችላል።

ልጆች ስልካቸውን ለረጅም ጊዜ እየተጠቀሙ ከሆነ እና እንቅልፋቸውን እንዲተኙ ከፈለግንም ስልኩን ወዲያውኑ ከሩቅ ሆነን በመቆለፍ እንዲተኙ ማድረግ እንችላላን።

በተጨማሪም ልጆች ኢንተርኔት ላይ የሚያፈላልጉትን ነገር ለመቆጣጣር፣ የሚጠቀሙትን መተግበሪያ ለማየት እና ለመቆጣጣር እንዲሁም ያሉበትን ቦታ ለይቶ ለማወቅም ያስችላል።

Families_3.png

“ፋሚሊ ሊንክ” መተግበሪያን ለመጠቀምም በመተግበሪያው በኩል ለልጃችን አዲስ የጎግል አድራኛ መክፈት የሚያስፈልገን ሲሆን፥ ልጆቹ በሚጠቀሙበት የአንድሮይድ ኤሌክትሮኒክስ በኩልም ወደ ጎግል አድራሻው መግባት ይኖርብናል።

መተግበሪያው አንድሮይት ኑጎት 7.0 እና ከቪያ በላይ በሆነ የአንድሮይድ ቨርዥን ላይ ብቻ የሚየሰራ ነው ተብሏል።

ፋሚሊ ሊንክ መተግበሪያ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ውስጥ ብቻ የሚሰራ ሲሆን፥ እድሜያቸው 13 ዓመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ያላቸው ወላጆች መተግበሪያውን በሙከራ ደረጃ እንዲጠቀሙት ተጋብዘዋል።

ጎግል የመተግበሪያው የሙከራ ጊዜውን እንዳጠናቀቀ እና አሁን በመጠቀም ላይ ካሉ ቤተሰቦች አስተያያት ከተቀበለ በኋላ በመላው ዓለም ላይ ላሉ ወላጆች እንደሚያቀርብ ታውቋል።

ምንጭ፦ https://fossbytes.com

በሙለታ መንገሻ