በጣት አሻራ የሚሰራ የኤ.ቲ.ም ካርድ ተሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣት አሻራ በመታገዝ የሚሰራና ከኤ.ቲ.ኤም ማሽን ገንዘብ ለማውጣት የሚረዳ ካርድ መሰራቱ ተነግሯል።

ካርዱ የክሬዲት ካርድ አቅራቢ በሆነው ማስተር ካርድ አማካኝነት የተሰራ ሲሆን፥ በደቡብ አፍሪካም ሁለት የተሳካ ሙከራዎች እንደተደረገበት ተነግሯል።

አዲሱ የማስተር ካርድ ቴክኖሎጂ ከዚህ ቀደም በሞባይል ክፍያ ሲፈፀም ካለው አሰራር ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይህም ባለ ካርዶች በካርዳቸው አማካኝነት ክፍያ በሚፈፅሙበት ወቅት የግድ የጣት አሻራቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

credit_card_2.jpg

የማስተር ካርድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አጄይ ብሃላ፥ የጣት አሻራው ቴክኖሎጂ ካርዳችንን በምንጠቀምበት ጊዜ የበለጠ ደህንነት እንዲኖረን ያደርጋል ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ