የአውሮፓ ህብረት በፌስቡክ ላይ 110 ሚሊየን ዩሮ ቀጣት ጣለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ ዋትስአፕን በተመለከት “አሳሳች“ መረጃ መስጠቱን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት 110 ዩሮ ቅጣት ጥሎበታል፡፡

ፌስቡክ እንዲቀጣ ምክንያት የሆነው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 ፌስቡክ የዋትአፕን የመልክት አገልግሎት በገዛበት ወቅት “ትክክለኛ ያልሆነ“ መረጃ በመስጠቱ ነው ተብሏል፡፡

የህብረቱ ኮሚሽን እንዳለው፥ፌስቡክ የዋትስአፕ የመልእክት አገልግሎት በገዛበት ወቅት የፌስቡክ አድራሻን ወዲያው ከዋትስአፕ ጋር አጣምሮ መጠቀም እንደማይቻል ገልጾ ነበር፡፡

ከሁለት አመት በኋላ ግን የፌስቡክና የዋትስአፕ አድራሻዎችን በማቆራኘት መልእክት መለዋወጥ የሚቻልበትን ዘዴ ተግባራዊ አድርጓ፡፡

ፌስቡክ ስህተቱ የተፈጠረው ሆን ተብሎ አለመሆኑን ነው የገለጸው፡፡

እ.ኤ.አበ2014 ፌስቡክና ዋትስአፕ አገልግሎቶችን ወዲያውኑ በማጣመር አንድ ሰው የፌስቡኩ እና የዋትስአፕ የመልእክት አገልግሎቶችን በአንድ አድራሻ ወይም ማንነት ማግኘት እንደማይቻል ፌስቡክ ቢገልጽም ፥አገልግሎቱ ግን ቀደም ብሎ ይሰራ እንደነበር ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡

ቀጣቱ ፌስቡክ ለዋትስአፕ ከፍሎ ማጠናቀቅ የሚገባውን 19ቢሊን ዶላርን የሚጨምር አይደለም ነው የተባለው፡፡

የህብረቱ የንግድ ውድድር ኮሚሽነር ማርገሪት ቬስታገር የአሁኑ ውሳኔ የሚያሳየው ኩባንያዎች ሲዋሃዱ የህብረቱን ህግ ማክበር እንዳለባቸው ግልጽ መልእክት ያስተላልፋል ብለዋል፡፡

በዋትስአፕ/ፌስቡክ ጥምረት በተለያዩ ሀገራት ችግር በኩባንያው ላይ ችግር እየፈጠረ ይገኛል፡፡

ባለፈው ሳምንት የጣሊያን ጸረ-ውድድር ተቆጣጣሪ አካላት ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች የግል መረጃዎቻቸውን ለፌስቡክ እንዲያጋሩ በማድረጉ 3 ሚሊየን ዩሮ ቅጣት አስተላልፈዋል፡፡

የፈረንሳይ የመረጃ ጥበቃ ተቆጣጣሪ አካላት ደግሞ የተጠቃሚዎችን መረጃ ማጋራት እና የአሁን መገኛ የማሳወቂያ ስርአቱ የሀገሪቱን ደንብ የሚጥስ ነው በሚል 150 ሺህ ብር በፌስቡክ ላይ ቅጣት መጣሏ ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ


በእስክንድር ከበደ