ሁዋዌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን መከታተል የሚያስችሉ አዳዲስ መሳሪያዎች አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁዋዌ በህንድ ገበያ ያስተዋወቃቸው የሚጠለቁ መሳሪያዎች፥ ሁዋዌ ባንድ 2፣ ሁዋዌ ባንድ 2 ፕሮ እና ሁዋዌ ፊት(Huawei Fit) የሚባሉት ናቸው።

ሁዋዌ ባንድ 2 ፕሮ የአካል ብቃት በማድረግ ለሚሮጡበት ጊዜ፥ ትክክለኛውን ርቀት እና የፍጥነት መጠን የሚያሳይ ሲሆን፥ የምንሮጠውን መጠን ይመዘግባል ተብሏል።

ሁዋዌ ባንድ 2 ደግሞ የላቀ የእንቅልፍ ክትትል በማድረግ የእንቅልፍ ጥራት በመገምገም፥ በእንቅልፍ መረጃው ላይ ተመስርቶ ለተጠቃሚው የእንቅልፍ ማሻሻያ ይሰጣል ነው የተባለው።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለመከታተል ውጤታማ የሆኑት፥ ሁዋዌ ባንድ 2 በ70 ነጥብ 5 የአሜሪካ ዶላር፥ እንዲሁም ሁዋዌ ባንድ 2 ፕሮ ደግሞ በ107 ነጥብ 4 የአሜሪካ ዶላር ገበያ ላይ ቀርበዋል።

Huawei-Band-2-Band-2_3730.jpg

እንደ ተቀባይ ሰዓት ሆኖ የሚያገለግለውን ሁዋዌ ፊት የመሸጫ ዋጋም 153 ነጥብ 46 የአሜሪካ ዶላር ተቆርጦለታል።

የኩባንያው የደንበኞች ሽያጭ ምክትል ፕሬዚዳንት ፒ ሳንጄቭ፥ አዳዲሶቹ ሁዋዌ ፊት እና ሁዋዌ ባንድ 2 ከሁለት ወር በፊት በተዋወቀው ሆነር ባንድ 3 ገበያ የተገኘውን ስኬታማነት ለመተካት እንተጋለን ብለዋል።

 

 

 

ምንጭ፦http://zeenews.india.com