ሳምሰንግ የ5G ኔትዎርክን በጃፓን ፈጣን ባቡር ላይ ሞከረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳምሰንግ የ5G ኔትዎርክ በጃፓን ፈጣን ተንቀሳቃሽ ባቡር ላይ ስኬታማ ሙከራ ማካሄዱን አስታወቀ።

ግዙፉ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ እና የቻይና የቴሌ ኮሙዩኒኬሽንስ ኦፕሬተር (ኬ ዲ ዲ አይ) ሰሞኑን በሰዓት ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ በሚጓዘው ቧብር ላይ የ5G ኔትወርክ ገጥመው ሙከራ አድርገዋል።

ሁለቱ ኩባናያዎች በባቡሩ በተገጠመው የ5G ኔትወርክ 1 ነጥብ 7 ጊጋ ባይት መረጃ በሰከንድ መላክ መቻላቸውን እና የግንኙነት ሁኔታን በስኬት መሞከራቸውን ነው ያስታወቁት።

ከቶኪዮ አቅራቢያ በምትገኘው ሳቲያማ በምትባል ቦታ በተደረገው ሙከራ የሳምሰንገ የ5G ቴክኖሎጂ፣ የ5G የኔትዎርክ ራውተር እና የ5G ሬዲዮ ስኬታማነት ፍተሻ ተደርጎባቸዋል።

በዚህም የፈጣን ባቡር ተጠቃሚ ተጓዥችን ፍላጎት ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ነው የተነገረው።

በባቡሩ ውስጥ የሚጓዙ ሰዎች በተገጠመው 5G ኔትወርክ ተጠቅመው ጥራቱ 8K የሆነ ቪዲዮ ወደ ሚጠቀሙበት ቴክኖሎጂ መገልገያ ማውረድ ይችላሉ ብሏል ሳምሰንግ።

ጃፓን በፈረንጆቹ 2020 የ5G ኔትወርክን እና የቴክኖሎጂ ምርቶችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ነው።

ምንጭ፦ www.techworm.net