ጎግል አዲሱን አንድሮይድ 8.1 ኦሬኦ የስማርት ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል አዲሱን አንድሮይድ 8.1 ኦሬኦ የስማርት ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ለተጠቃሚዎች በይፋ ለቋል።

ጎግል የመጀመሪያውን አንድሮይድ 8.1 ኦሬኦ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን በፒክስል 2 ስማርት ስልኩ ላይ መልቀቁም ተነግሯል።

ሁሉም የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች አንድሮይድ 8.1 ኦሬኦ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን መጠቀም እንዲችሉ በነፃ እንደሚያቀርብም ጎግል አስታውቋል።

አዲሱ አንድሮይድ 8.1 ኦሬኦ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከዚህ ቀደም ካሉት ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በተሻለ ማሻሻያዎች የተደረጉለት እና በቀላሉ ለመረጃ ጠላፊዎች እንዳይጋለጥ የሚረዳ ደህንነት እንዳለውም ታውቋል።

አንድሮይድ 8.1 ኦሬኦ በአነስተኛ ዋጋ በሚገዙ እና ከ1 ጊጋ ባይት ራም በታች ባላቸው ስልኮች ላይ ጭምር እንዲሰራ ተደርጎ መሰራቱም ተገልጿል።

ምንጭ፦ fossbytes.com