ሳምሰንግ 396 ሴንቲ ሜትር ስፋት ያለው ቴሌቪዥን በላስቬጋሱ የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ግዙፍ የተባለውን ባለ 396 ሴንቲ ሜትር ስፋት ቴሌቪዥን በላስቬጋስ እየተካሄደ ባለው የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ አቀረበ።

ቴሌቪዥኑ ኤል.ኢ.ዲ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ሲሆን፥ ይህም ከፍተኛ የስክሪን ጥራት እንዲኖረው ያደርጓል ነው የተባለው።

ይሁን እንጂ በአምራች ዘርፎች ለማምረት በጣም ውድ እንደሚሆን በአውደ ርእዩ የተገኙ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ገልፀዋል።

_99515920_38858603134_8391ab5d15_h.jpg

በላስቬጋስ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ከመኪና እስከ ቤት ውስጥ አገልጋይ ሮቦቶችን ያካተተው ይህ አውደርዕይ የዓለምን ቀልብ ስቧል።

አሁን ሳምሰንግ ያቀረበው አዲስ የቴሌቪዥን ምርት ዋጋ ዝርዝርን ኩባንያው ይፋ አላደረገም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ