450 ኪሎ ግራም የሚመዝነው በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ለእይታ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና በአውሮፓውያኑ 2019 ገበያ ላይ ይውላል የተባለው 450 ኪሎ ግራም የሚመዝነው በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀስ ነገር ግን ፍጥነቱ አነስተኛ የሆነ ተሽከርካሪ ለእይታ ቀረበ ነው።

በቻይና ሻንጋይ ባህላዊ ሙዚየም ውስጥ ለእይታ የቀረበው ተሽከርካሪ፥ በኤክስ ኢ ቪ እና ፖሊሜኬር የተባሉት ኩባንያዎች የተመረተ አዲስ ፈጠራ ነው ተብሏል።

ሞዴሉ አዳዲስ ፈጠራ የተካተቱበት ሲሆን፥ በ57 አካላት የተዋቀረ ነው።

450 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ ተሽከርካሪ፥ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀስ በመሆኑ የካርቦን መጠን እንዲቀንስ ያግዛል ተብሏል።

በዚህም አዲሱ ሞዴል፥ እስካሁን ድረስ በአውሮፓ ሀገሮች 7 ሺህ ትዕዛዞችን አግኝቷል ነው የተባለው።

አሁን ላይ ለአውደ ርዕይ የቀረበው ይህ በኤሌከትሪክ የሚንቀሳቀስ ዝቅ ባለ ፍጥነት የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ፥ ከሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት 2019 ሚያዚያ ወር ጀምሮ በቻይና ገበያ በስፋት ይቀርባል ተብላል።

 

 

 

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን