ዋትስአፕ በስህተት የተላከ መልእክት ለማጥፋት የሚያስችል አገልግሎት ወደ አንድ ሰአት አሻሻለ


አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋትስአፕ በስህተት የተላከ መልእክት ለማጥፋት የሚያስችል አገልግሎት ወደ አንድ ሰአት ማሻሻሉን አስታወቀ።

የፌስቡክ ኩባንያ መተግበሪያ የሆነው ዋትስአፕ ባለፈው የፈረንጆች ጥቅምት ወር ላይ በስህተት የተላከው መልእክት በ7 ደቂቃዎች ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል አገልግሎት አስተዋውቆ ነበር።

 ይህ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት “Delete for everyone” የሚል አገልግሎት፥ የፅሁፍ፣ የድምጽ፣ የቪዲዮ እና ሌሎች መልእክቶችንም ለማጥፋት የሚያስችል ነው።

 

ይህም በቡድንን ወይም በሁለት ሰዎች መካከል በግል በሚደረግ የመልእክት ልውውጥ ወቅት በስህተት የተላከን መልእክት ለይቶ ለማጥፋት የሚያስችል ነው።

በመሆኑም ዋትስአፕ በአሁኑ ወቅት ይህ የጊዜ ገደቡ ወደ 1 ሰአት ከስምት ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ ያራዘመው ሲሆን፥ ጊዜው ለምን እንዳራዘመው ግን የተባለ ነገር የለም።

ዋትስአፕ ከሌሎች አቻ ተቋማት አንፃር ሚስጥራዊ መልዕክት መለዋወጫ እንደሌለው ይነገራል።

ይህም ማሻሻያ ጊዜያዊ የመልዕክት መለዋወጫ እድል እንዲኖር ያስቻለ ነው ተብሏል።

በስህተት የተላከን መልእክት ለይቶ ለማጥፋት የሚያስችል አዲሱ ማሻሻያ በላኩት ፅሁፍ በመፀፀት ለማስተካከል ለሚፈልጉ ሰዎች መልካም እድል ይፈጥራል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ዘቨርጅ