ለ6 ዓመታት ሳይታወቅ የቆየውና በራውተር በኩል ኮምፒውተራችንን የሚያጠቃው ቫይረስ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካስፐርስኪ የምርምር ማእከል የሚገኙ ተመራማሪዎች “ስለሊንግሾት” የተባለ አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

ተመራማሪዎቹ አዲስ ያገኙት የኮምፒውተር ቫይረስም ራሱን ደብቆ ለስድስት ዓመታት ሊቆይ የሚችል መሆኑን ነው ተመራማሪዎቹ የተናገሩት።

ቁጥሩ በእውን ባይታወቀም ቫይረሱ እስካሁን በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ 100 የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ላይ ጥቃት ማድረሱንም አስታውቀዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2012መፈጠሩ የተነገረለት ይህ የኮምፒውተር ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ግን ከ6 ዓመታት በኋላ በያዝነው የፈረንጆቹ 2018 ጥር ወር ላይ ነው።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ ቫይሰሩ ውስብስብ በሆነ መንገድ በመሰራቱ ራሱን በቀላሉ የሚደብቅና በቀላሉ የማይገኝ ነው።

ቫይረሱ ኮምፒውተራችንን ከሚያጠቃበት መንገዶች ውስጥ አንዶ ደግሞ “ማይክሮቲክ (MikroTik)” በተባሉ የኢንተርኔት ማከፋፋያ ራውተሮች አማካኝነት ነው ተብሏል።

Slingshot_1.png

ቫይረሱ አንዴ ወደ ኮምፒውተራችን ከገባ በኋላም የዩ.ኤስ.ቢ ግንኙነቶችን ጨምሮ የኪቦርድ፣ የክሊፖቦርድ ዳታ፣ ኔትዎርክ ዳታ፣ ስክሪን ሾት እና የይለፍ ቃል ወይም ፓስወርድ መረጃዎችን በቀላሉ ይሰበስባል።

“ስለሊንግሾት” የኮምፒውተር ቫይረስን በምን መልኩ መከላከል ይቻላል የሚለው ላይ እየሰሩ የሚገኙት ተመራማሪዎቹ፥ ለጊዜው ያለው አማራጭ የኢንተርኔት ማከፋፈያ ወይም ራውተራችንን በአዲስ መተካት ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ fossbytes.com