ሶፍትዌር አበልፃጊው ግለሰብ በአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ ከስራው ተባረረ

አዲስ አበባ፣ሃምሌ፣4፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)አርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ በአሁን ወቅት በባንኮች፣ ባቡር ጣቢያ፣ ሆቴል እና ሌሎች በርካታ ተቋማት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉት ይታወቃል።

በዚህም ምክንያት ወደ ፊት አርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ የሰውን ስራ ሙሉ በሙሉ ተከተው ሊሰሩ ይችላሉ የሚል ስጋ በበርካቶች ዘንድ ይነሳል።

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ኢብራሂም ዲአሎ የተባላ ሶፍትዌር አበልፃጊው በቀደሞው ስራ አስኪያጁ በአዲስ የኮምፒውተር ስርዓት የስራ ውሉ ባለመታደሱ ግለሰቡ በማሽኑ ትዕዛዝ ከስራ እንደተባረረ እና በጥበቃዎች ከስራ ቦታው እንዲወጣ መደረጉም ተነግሯል።

ግለሰቡ በማሽኑ ትዕዛዝ ከስራ በተሰናበተበት ወቅት ስራ አስኪያጁ ምን ማድረግ አልቻሉም ተብሏል።

ኢብራሂም ዲአሎ የተባለው ሶፍትዌር አበልፃጊ ግለሰብ ስራ አስኪያጁ እና ዳይሬክተሩ ችግሩ በተፈጠረበት ወቅት ምንም ማድረግ እንዳልቻሉና አቅም እንዳልነበራቸው አስታውቋል።

ኢብራሂም ዲአሎ ይህ ሁኔታ ኩባንያዎች በአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ እና በተመሳሳይ ማሽኖች ጥገኛ መሆን እንደሌለባቸው ያሳየና ትምህርት ሊወሰድበት የሚገባ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቡ በተቋም ውስጥ ለሶስት ዓመት የሚቆይ የስራ ውል ያለው ሲሆን ላለፉት ስምንት ወራት በኩባንያው በሶፈትዌር አበልፃጊነት ሲሰራ እንደቆየና በቅርቡ ለስራ መግቢያ የሚጠቀምበት ቁልፍ መስራት ማቆሙን አስታውሷል።

ምንጭ፡- techworm