በባዶ ሆድ ቡና ቢጠጡ ሰውነት ላይ ምን ይከሰታል?

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ማለዳ በባዶ ሆድ ቡና የመጠጣት ልማድ አለዎት?

ይህ አይነቱ ልማድ ካለብዎት ምግብ ሳይመገቡ በባዶ ሆድ ቡና መጠጣት ጉዳት ያስከትላልና ቆም ብለው ያስቡበት።

ምንም ያክል የቡና ሱሰኛ ቢሆኑም እንኳን ይህን መሰሉን ልምድ እንዲያቆሙም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

እስኪ ባበዶ ሆድ ቡና ቢጠጡ ምን እንደሚፈጠር ይመልከቱ።

ከፍተኛ መጠን ያለው አሲድ፦ ሆድ ውስጥ ምግብ እንዲፈጭ የሚያደርገው ሃይድሮክሎሪክ አሲድ ይገኛል፤ ይህ አሲድ ሆድ ባዶ ሲሆን ስራ የለውምና በብዛት ይረጫል።

በባዶ ሆድ ቡና መጠጣት ደግሞ የአሲዱን መጠን በመጨመር በተለይም ጨጓራ ላይ ጉዳት ያስከትላል።

ልብ አካባቢ የማቃጠልና ህመም ስሜት፣ አንጀት አካባቢ ከፍተኛ ህመም፣ በትንሹ የአንጀት ክፍል ላይ የሚከሰት ጉዳት፣ የጨጓራ ህመምና የማቃጠል ስሜት ደግሞ በዚህ ወቅት የሚከሰቱ ናቸው።

የስርዓተ ምግብ መፈጨት መስተጓጎል፦ በባዶ ሆድ አነቃቂ ነገሮችን መውሰድ የስርዓተ ምግብ መፈጨትን በማስተጓጎል ችግር ይፈጥራል።

የጠጡት ቡና ኩላሊጠ አካባቢ የሚገኙና በፍርሃት ጊዜ ሆርሞን የሚያመነጩ እጢዎችን ሃላፊነት በዚህ ጊዜ ይከውናል።

እነዚህ እጢዎች የሚያመነጩት ሆርሞን በዚህ ወቅት ሲሆን፥ የልብ ምት እና የደም ግፊት መጠንን ይጨምራል።

ጉበት ደግሞ ለሰውነት ውስጥ ጡንቻዎች ሃይል ለመስጠት ሲል፥ ግሉኮስ (በደም ውስጥ የሚገኝ ስኳርን) በብዛት ያሰራጫል።

ጨጓራም ምግብ መፍጨቱን አቁሞ ሃይሉን ይበልጥ ወደሚያስፈልገው የሰውነት ክፍል ይልካል።

በዚህ ጊዜም የሆድ መነፋት፣ የሆድ አካባቢ ህመምና እንግዳ ስሜት ይሰማል፤ ጨጓራም በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል።

ጨጓራም ሃይሉን ስለሚያጣ የስርዓተ ምግበ መፈጨት በዚህ ጊዜ ይስተጓጎላል፡፡

ጭንቀት፦ ማለዳ በባዶ ሆድ ሲሆኑ የታችኛው የአዕምሮ ክፍል ሴሮቶኒን (የደስታ፣ ጭንቀት እና ሌሎች ስሜቶችን የሚወስን ሆርሞን) መስበር መቻል አለበት።

በባዶ ሆድ ቡና ሲጠጡ ደግሞ የታችኛው የአዕምሮ ክፍልም ሴሮቶኒንን እንዳይሰብር ያደርገዋል፡፡

ይህ ሆርሞን በዚህ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ኮርቲሶልን በማመንጨትም ጭንቀትና አለመረጋጋትን ያስከትላል።

መቁነጥነጥ፣ መበሳጨት፣ ትዕግስት አልባ መሆንና የሰውነት ድካምም በዚህ ወቅት ይስተዋላሉ።

ሰውነት ላይ የፈሳሽ እጥረት ይከሰታል፦ በባዶ ሆድ ቡና ሲጠጡ ከሰውነት በርካታ መጠን ያለው ፈሳሽ እንዲወገድ ያደርጋል።

ይህ ሲሆን ደግሞ ሰውነት ላይ የፈሳሽ እጥረትን በመፍጠር ድርቀትን ያስከትላል።

የሆርሞን ቁጥር መቀነስ፦ በእርግጥ ቡና መጠጣት የርሃብ ስሜትን የመቀነስና እንዳይሰማ የማድረግ አቅምም አለው፤ ይህ መልካም ባይሆንም።

በዚያው ልክም ለምግብ ፍላጎት መቀነስ ምክንያት እንደሆነም ይታመናል፤ በተለይ በባዶ ሆድ ሲሆን ለመብላት ፍላጎት ያጣሉ።

ማለዳ በባዶ ሆድ ቡና ከጠጡ ደግሞ ቁርስ እንዳይበሉ ያደርጋል፤ ቁርስ አለመመገብ ደግሞ የሰውነትን ሃይል ያዛባል።

በዚህ ወቅትም ሴሮቶኒን እየጠፋ ይሄዳል፤ ከልክ በላይ የደስታና የመረጋጋት ስሜት ደግሞ በዚህ ወቅት ይፈጠራል።

ይህ ደግሞ ምሽት ላይ ለእንቅልፍ እጦት ይዳርጋል፤ ለእንቅልፍ የሚረዳው የሜላቶኒን እጥረት ይከሰታልና።

ሰውነት ሴሮቶኒንን ምሽት ላይ ወደ ሜላቶኒን ይቀይረዋል፤ በባዶ ሆድ ቡና በጠጡ ቁጥር ግን የዚህ ሆርሞን ቁጥር ስለሚቀንስ የሜላቶኒን እጥረት ይከሰታል።
ይህ ደግሞ ለእንቅልፍ እጦት ይዳርጋል።

እናም መልካም እንደሆነ ከሚያስቡት የማለዳ ልማድ ይህ አደገኛ ነውና ያስወግዱት፤ ሱሰኛ ቢሆኑም ቡና መጠጣት ካስፈለገዎት ምግብ ከተመገቡ በኋላ ሊሆን እንደሚገባም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

 

ምንጭ፦ humannhealth.com/

android_ads__.jpg