ለጠንካራ እና ለስላሳ ቆዳ የሚመከሩ ምግቦች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰዎች ቆዳቸው ጤነኛ እንዲሆን በርካታ ነገሮችን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ተመራማሪዎች ከዚህ በታች የቀረቡትን ምግቦች በየቀኑ መጠቀም ለቆዳ ጥንካሬ እና ልስላሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ኣላቸው ብለዋል፡፡

1. ቀይ ቃሪያ

red_peprs.jpg

ቫይታሚን ሲ በፊት ቆዳ ላይ መቀባት ወይም በምግብ መልኩ መውሰድ ለቆዳ መልካም እንደሆነ ይመከራል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቫይታሚን ሲ የቆዳ መሸብሸብንና ድርቀትን ይከላከላል፡፡

ለዚህ ደግሞ ቀይ ቃሪያዎች በቫይታሚን ሲ ይዘታቸው ከፍተኛ በመሆናቸው ሰዎች እንዲመገቧቸው ይመከራል፡፡

የቫይታሚን ሲ መጠናቸው ከብርቱካን ሶስት እጥፍ ይበልጣል ተብሏል፡፡

2. ውሃ

water.jpg

ውሃ ለሰው ልጅ ህይወት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ሀቅ ነው፤ ሆኖም ጥናቶች እንደሚሉት በየቀኑ የሚወሰደውን የውሃ መጠን ከፍ ማድረግ የቆዳን ጤና ይጠብቃል፤ ወዝ ያለው እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል፡፡

ጥናቶች በየቀኑ ሁለት ሊትር ውሃ የሚጠጣ ሰው ከቀን ወደ ቀን በተሻለ መልኩ የቆዳውን ጤና እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል፡፡

3. የለውዝ ዘይት

peanut_oil.jpg

በፈረንጆች 2007 የተሰራ አንድ ጥናት ሊኖሊክ አሲድ የቆዳን እድሜ ጤናማነት ያሻሽላል የሚል ግኝት ይፋ አድርጎ ነበር፡፡

ሊኖሊክ አሲድ የሚባለው ባለብዙ ንጥረነገር ወይም ም ኦሜጋ-6 ፈሳሽ አሲድ ሲሆን የሚገኘውም በለውዝ ዘይት ውስጥ ነው፡፡

4. አረንጓዴ ሻይ

green_tea.jpg

አረንጓዴ ሻይ አይጣፍጥም የሚል ወቀሳ ቢቀርብበትም ለሰው ልጅ ጤና በእጅጉ ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በ2010 የተሰራ አንድ ጥናት በየቀኑ አረንጓዴ ሻይ የሚጠጡ ሰዎች በቆዳቸው ላይ መልካም የሆነ የቀርፊት ወዝ፣ እና
ተለጣጭነት እንዲሁም ጥንካሬ ይኖራቸዋል የሚል ውጤትይ ፋ አድርጓል፡፡

5. አቮካዶ

Avocado-Bacon-Eggrolls-2.jpg

አቮካዶን በብዛት መመገብ የተለመደ ወይም ያልተለመደ ሊሆን ይችላል፡፡

በጃፓን የተደረገ አንድ ጥናት ሁሉም ስብ ያላቸው ምግቦች ፈሳሽም ሆኑ ጠጣር ነገሮችን በመጠኑ መመገብ ለቆዳ ጤናማነት አመቺ መሆናቸውን አሳይቷል፡፡

በተለይም ፈሳሽ ነጥረነገርን በውስጡ የያዘውን አቮካዶን መመገብ የቆዳን ልስላሴ ከፍ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

 

 

 

ምንጭ፡-http://www.refinery29.uk