ወተት መጠጣት ለልብ ህመም የመጋለጥ አድልን እንደሚቀንስ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት ወተት የልብ ህመም ተጋላጭነተን በመቀነስ ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።

ተመራማሪዎች በቅርብ ባወጡት የጥናት ውጤት በደማቸው ውስጥ አነስተኛ የካልሺየም ንጥረ ነገር መጠን ያለቸው ሰዎች በቀላሉ ለልብ ድካም ሊጋለጡ ይችላሉ፤ ልባቸውም በድንገት ስራውን ማቆም ይችላል ብለዋል።

ለእንዲህ አይነት የልብ ጤንነት ችግር የመጋለጥ እድልን ለመቀነስ ወተትን አዘውትሮ መጠጣት እና እንደ አይቤ ያሉ የወተት ተዋእጾዎችን አዘውትሮ መውሰድ መልካም መሆኑን የአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ካርድሲናይ የልብ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

የልብ ምት በድንገድ መቆም ልባችን ወደ ሰውነታችን የሚያሰራጨውን ደም በድንገት ሲያቋርጥ የሚከሰት ነው።

ይህ ችግር በህክምና በአፋጣኝ መፍትሄ ካላገኘም ታማመዊው በደቂቃዎች ውስጥ ህይወቱ ሊያልፍ ይችላል።

በዚህ የጤና ችግር በእንግሊዝ ብቻ በየዓመቱ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት ያልፋል የተባለ ሲሆን፥ በአሜሪካ ደግሞ ቁጥሩ ከዚህ በአራት እጥፍ ይበልጣል ነው የተባለው።

በደም ውስጥ የካልሺየም መጠን መቀነስ ለልባችን ድንገኛ የስራ ማቆም እንደሚያጋልጥ ያረጋገጠው አዲሱ ጥናት፥ ከዚህ ችግር ለመውጣት ደግሞ የተወት ተዋጽኦዎችን አዘውትሮ መልካም ነው ብሏል።

ወተት መጠጣት እና እንደ አይቤ ያሉ የወተት ተዋጽኦዎችን በቁርሳችን ወስጥ አካተን መጠቀም ለልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ከመቀነስ ባሻገር ቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk