ለውዝ የልብ ህመም ተጋላጭነትን ከመቀነስ አንፃር…

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበርካታ ንጥረ ነገሮች የበለጸገው ለውዝ (ኦቾሎኒ) በርካታ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በብዛት ሲነገርለት ቆይቷል።

ለውዝ በተፈጥሮ ፋይቶስትሮል፣ ፋይበር እና ፎሊክ አሲድ እንዲሁም በፋቲ አሲድ በተባሉ ንጥረ ነገሮች በለጸገ ነው።

በመሆኑ ሁሌም ቁርስ ስንመገብ የተወሰወነ ግራም ለውዝ አካተን ከወሰድን በውስጣችን ያለውን መጥፎ የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ በማድርግ ለልብ ህመም ተጋላጭነታችንን ይቀንሳል።

ከሰሞኑ የወጣ አዲስ ጥናትም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሲሆን፥ ለውዝን አዘውርቶ መመገብ ለልብ ጤንነት ወሳኝ መሆኑን ይጠቁማል።

ከዚህ ድምዳሜ ላይ የተደረሰውም በአሜሪካ በ210 ሺህ ሰዎች ላይ ለ32 ዓመታት ሲካሄድ የነበረው ክትትል እና ጥናት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

ጥናቱን ያካሄዱት ተመራማሪዎችም ለውዝን በእለት ተእለት መግባቸው ውስጥ አካተው የሚመገቡ ሰዎች ለልብ ህመም ያላቸው ተጋላጭነት ከሌሎች አንጻር ሲታይ ቀንሶ መታየቱን ለይተዋል።

የጥናቱ ውጤትም ሰዎች በእለት ተእለት ምግባቸው ውስጥ የሚሰውዱትን የለውዝ መጠን እንዲጨምሩ የሚገፋፋ መሆኑን የጥናት ቡድኑ መሪ ማርታ ጉሳች ፌር ተናግረዋል።

በአሜሪካ የጤና ኢኒስቲትዩት የገንዘብ ድጋፍ አድራጊነት በሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን ትምህረት ቤት የተሰራው ጥናት ለዝው የሚመገቡ እና የማይመገቡ ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነትን ተመልክቷል።

በዚህም መሰረት ለውዝን የሚመገቡ ሰዎች ከማይመገቡ ሰዎች ጋር በሚነጻጸሩበት ጊዜ የተመጋቢዎች ለልብ ህመም የመጋለጥ እድል በ20 በመቶ ቀንሶ ተገኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በጥናቱ ለውዝን መመገብ የስትሮክ (ወደ አእምሮ የሚገባ ደም መቋረጥ) የጤና ችግርን ከመከላከል ያለውን ሚናም ተመልክቷል።

በዚህም ለውዝን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች ለስትሮክ (ወደ አእምሮ የሚገባ ደም መቋረጥ) የጤና ችግር የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Health