የተበከለ አየር አዲስ በተወለዱ 17 ሚሊየን ህፃናት የሳንባና የአንጎል እድገት ላይ ችግር ፈጥሯል-ዩኒሴፍ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የተበከለ አየር አዲስ በተወለዱ 17 ሚሊየን ህፃናት የሳንባ እና የአንጎል እድገት ላይ ችግር መፍጠሩን የተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።

ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ከ12 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህፃናት የሚኖሩት በደቡብ እስያ ሀገራት መሆኑ ነው የተመላከተው።

ይህም መረጃ የተዘጋጀው በአየር ብክለት ከፍተኛ ጫና የደረሰባቸውን አካባቢዎች በሳተላይት ምስሎች በመመዝገብ ነው።

ዩኒሴፍ የአየር ብክለቱ በዓለም የጤና ድርጅት ለንፁህ አየር ብሎ ካስቀመጠው መስፈርት ከበለጠ ለህፃናት አስጊ መሆኑን ጠቁሟል።

ብክለቱ ህጻናቱ ንፁህ አየር እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል፥ የመተንፈሻ አካላቸውን ይጎዳዋል ብሏል ዩኒሴፍ።

በአስም፣ የሳንባ ምች እና ሌሎች ተመሳሳይ ህመሞች እንዲጠቁ የማድረግ አቅም እንዳለውም የህጻናት አድን ድርጅቱ ገልጿል።

የህጻናት የመጀመሪያዎቹ 1 ሺህ ቀናት የአንጎል እድገት ጤናማነት በቀሪው የህይወት ዘመን እድገታቸው እና የመማር ችሎታቸው ላይ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

ሆኖም የአየር ብክለት መጨመር ለህፃናቱ ጤንነት አሳሳቢ ስለሆ ሊታሰብበት እንደሚገባ ዩኒሴፍ ጥሪ አቅርቧል።

 

 

 

ምንጭ፦doctor.ndtv.com