የአቨካዶ ዘይት ለፀጉር እድገትና ውበት የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጥናቶች የስብ ይዘት እና ፀረ የሰውነት ማቃጠል ይዘት ያላቸው እንዲሁም ማዕድናት ለፀጉር እና ለቆዳ ጤንነት የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮች እንደሆኑ ጠቁሟል።

ለዚህም ባለሙያዎቹ የአቨካዶ ዘይት በተለያዩ መአድናት እና ቪታሚኖች የበለፀገ ሲሆን፥ ለፀጉር እድገት፣ ውበት እና ሌሎችንም ያለው አስተዋፅኦ ማወቅ ጠቃሚ ነው ብለዉናል።

የአቮካዶ ዘይት ጥቅሞች

avocado-oil-benefits-for-hair.jpg

የአቨካዶ ዘይት በራሱ ማዕድናት፣ አስፈላጊ የስብ አሲዶች እንዲሁም በቫይታሚን ኤ፣ ቢ-5 እና ኢ የበለፀገ በመሆኑ፥ በፍሬ ወይም ዘይት ለፀጉርዎ መጠቀም ይችላሉ።
ይህም ፀጉርዎን ጠንካራ ለማድረግ ከፈለጉ አቨካዶ መመገብ የተሻለ መንገድ ነው ተብሏል።

በዚህም ይህ የአትክልት አይነት ስንመገብ በቫይታሚን ቢ-5 እና ቫይታሚን ኢ የበለፀገ በመሆኑ በፀጉር እድገትና ውበት የተሻለ ጠቀሜታ አለው።

በተጨማሪም የአቨካዶ ቅባት ለፀጉርዎን መጠቀም ፀጉር ከድርቀት ለመከላከል፣ የተጎዳውን መልሶ ለመጠገን እና ለፀጉር ጥንካሬ ይረዳል።

በአውሮፓውያኑ 2015 የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፥ በአቨካዶ ዘይት ውስጥ የሚገኙት ማዕድናት ፀጉር እንዳይሰበር ሊከላከል የሚችል ይዘት አላቸው።

አቨካዶ ለፀጉር እድገት እንዴት መጠቀም እንችላለን?

avocado-oil-for-hair.jpg

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የወይን ጠጅ እና የናና ዘይቶች ፀጉር እንዲያድግ ይረዳሉ።

ለዚህም 28 ግራም የአቮካዶ ዘይት ከሶስት እስከ ስድስት ጠብታ የወይን ጠጅ እና የናና ቅጠል ዘይት በመጨመር መጠቀም ይቻላል ነው የተባለው።

በተጨማሪም የአቨካዶ ዘይት በመጠቀም ቆዳዎ ማሸት ያለው ጠቀሜታ የላቀ ነው፤ ይህም ጤናማ የደም ዝውውር እንዲኖር ያደርጋል።

እነዚህ ውጤቶችም የፀጉር መሰባበር ለመከላከል ሊረዱ ይችላሉ ተብሏል።

ይሁን እንጂ በፀጉርዎ ላይ የአቮካዶ ዘይት በብዛት ከተጠቀሙ ዘይቱን እስኪለቅ ድረስ ከኬሚካል ነፃ በሆነ ሻምፖ በደንብ መታጠብ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎቹ ምክራቸው ለግሰዋል።

 

 

ምንጭ፦www.healthline.com