ተመራማሪዎች ከማሰብ ክህሎት ጋር የተያያዙ ከ500 በላይ በራሄዎችን ለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከማሰብ ክህሎት ጋር የተያያዙ 538 በራሄዎችን /ጂን/ መለየታቸውን የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች አስታወቁ።

የኤደንበርግ፣ የሳውዝሃፕተን እና የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ 240 ሺህ ሰዎች ዘረምል በመሰብሰብ የትኛዎቹ የበራሄ /ጂን/

የዓይነቶች ከማሰብ ችሎታ ጋር እንደሚያያዙ አጥንተዋል።

በተጨማሪም አንዳንድ ከማሰብ ችሎታ ጋር ግንኙነት ያላቸው በራሄዎች ረዥም ዕድሜ ከመኖር ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በጥናቱ ይፋ ሆኗል።

የኤደንበርግ ዩኒቨርስቲይ ተማራማሪ ፕሮፌሰር ኢያን ዴሪይ በሰው ልጆች የማሰብ ልዩነት ውስጥ አካባቢ እና በራሄ የራሳቸውን ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም ገልጸዋል።

ፕሮፌሰሩ ይህ ጥናት የትኛው በራሄ የማሰብ ክህሎት እንዳለው እንዲሁም የጤናና የማሰብ ችሎታ ግንኙነትን አመላክቶናል ብለዋል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ዥንዋ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ አብረሃም ፈቀደ