በቀዶ ህክምና ላይ ያሉ ህሙማን የደም ዝውውር ፍጥነት ሊቀንስ ስለመሆኑ የሚጠቁም ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ላይ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ5፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ)በቀዶ ህክምና ላይ ያሉ ህሙማን የደም ዝውውር ፍጥነት ሊቀንስ ስለመሆኑ የሚጠቁም ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ላይ ውሏል ተብሏል።

በቀዶ ህክምና ላይ ያሉ ሰዎች የደም ዝውውር ከቀነሰ ለደም መርጋትና ደም ለተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ያለመድረስ ችግር እንደሚጋለጡ የአሜሪካ የሰመመን ሃኪሞች ማህበር መረጃ አመላክቷል።

ቀደም ሲል የቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚያገኙ ህሙማን ችግሩ እንደተከሰተ ህክምናውን ያገኙ የነበረ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፥ አዲሱ ቴክኖሎጂ ችግሩ ከመከሰቱ 15 ደቂቃ በፊት ቀድሞ ምልክት የሚሳይና 84 በመቶ ያህል ውጤታመ መሆኑ ነው የተገለጸው። 

ህሙማኑ በቀዶ ህክምና ላይ ሳሉ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ቀደም ብሎ የህሙማኑ የደም ዝውውር ፍጥነት ሊቀንስ ስለመሆኑ የሚጠቁመው የአዲሱ መሳሪያ ግኝት ባለሞያወቹ ቅድመ ዝግጅትት በማድረግ ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ሎሳንጀለስ ተቋም የሰመመን ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ማክሲሜ ካኔሰን ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂው ለልብ ህሙማንን፣ ከፍተኛ የኩላሊት ችግር ላለባቸውና በተመሳሳይ ሁኔታ ለሞት አደጋ ሊጋለጡ የሚችሉ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ያስችላል ተብሏል።

ተመራማሪዎቹ በ1ሺህ334 ህሙማን ላይ ለ545 ሺህ 959 ደቂቃዎች ያህል በዚሁ ቴክኖሎጂ ባደረጉት ክትትል የህሙማኑ የደም ዝውውር ዝቅተኛ ሊሆን ስለመሆኑ ቴክኖሎጂው በትክክል ማመለከት መቻሉን ማረጋገጣቸው ነው የተገለጸው። 

የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደርም ለዚሁ ቴክኖሎጂ እውቅና መስጠቱ ታውቋል።

 

 

 

ምንጭ፦ upi.com

 

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ