Fana: At a Speed of Life!

4 ልጆቿን በጫካ ውስጥ ስታሳድግ ለነበረች እናት የመኖሪያ ቤት ተበረከተላት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 4 ልጆቿን በጫካ ውስጥ ስታሳድግ ለነበረች እናት በ478 ሺህ ብር ወጪ የተደረገበት የመኖሪያ ቤት እና የቤት ቁሳቁስ ተበረከተላት፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 4 ልጆቿን በጫካ ውስጥ ስታሳድግ ለነበረች ለወይዘሮ ሰሚራ ይልማ የመኖሪያ ቤትና ሙሉ የቤት ቁሳቁስ አበርክቷል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መለስ አለም የተገኙ ሲሆን÷ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከወረዳ 1 አስተዳደር ጋር በመተባበር በ478 ሺህ ብር ወጪ ለወይዘሮ ሰሚራ ይልማ የመኖሪያ ቤትና የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በከተማዋ አስቸጋር ህይወትን የሚመሩ ወገኖች መኖራቸውን አቶ መለስ አለም ቤቱን ባስረከቡበት ወቅት የገለጹ ሲሆን÷ ̎በአቅማችን መድረስ ከቻልን የብዙዎችን ህይወት እንቀይራለን፣ ለዚህ ቤተሰብ ሀገር ደርሷል ሀገር ማለት ቤተሰብ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የሁላችንም ሀገር የሆነችውን ኢትዮጵያን ሰላም ለመጠበቅ እንጠንክር የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ረዲ በበኩላቸው÷ በበጎ ተግባሩ የተሳተፉትን አመስግነው መረዳዳትና መተጋገዝ ከቻልን የበርካቶችን ህይወት እንደምንቀይር ይህ ተግባር ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ወይዘሮ ሰሚራ በበኩላቸው÷̎የሀገር ውለታ አለብኝ ልጆቼ ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ እንዲሆን አንፃቸዋለሁ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.