45 ቡና ላኪዎች ለወጪ ንግድ ማቅረብ የሚጠበቅባቸውን ቡና አላቀረቡም - የንግድ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንግድ ሚኒስቴር በተያዘው ዓመት 45 ቡና ላኪዎች ቡና ገዝተው ለወጪ ንግድ ማቅረብ ሲገባቸው አለማቅረባቸውን ገለፀ፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አያና ዘውዴ ላኪዎቹ ለውጭ ገበያ መላክ የነበረባቸው የቡና መጠን የተለየ ሲሆን፥ ያልላኩበት ምክንያት ተጣርቶ በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል ብለዋል።

ከግብርና ምርቶች ከፍተኛ የወጪ ንግድ ድርሻ በሚይዘው ቡና ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን መፍታትም ቅድሚያ እንደሚሰጠው ነው ሚኒስትር ዴታው የገለጹት።

በምርት ርክክብ፣ በደረጃ አሰጣጥና በናሙና አወሳሰድ ወቅት የሚከሰቱ የሥነ-ምግባር ችግር የታዩባቸውን አመራሮችና ፈፃሚ አካላትን በመለየት እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ በየ15 ቀኑ ከፌዴራል ፖሊስና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በቡናና ሻይ ምርትና ግብይት ባለሥልጣን ላይ የኦዲት ግምገማ እንደሚያደርግ ም ነው ያብራሩት።

 

ምንጭ፡- ኢዜአ