የኢትዮጵያ አየር መንገድ 262 የአቪዬሽን ባለሞያዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ያሰጠለናቸውን 262 የአቪዬሽን ባለሞያዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

ከተመራቂ ሰልጣኞች ውስጥም 50 ፓይለቶች እና 66 ቴክኒሺያኖች የሚገኙበት ሲሆን፥ 34 የውጭ አገር ዜጎችም ከተመራቂዎቹ ውስጥ ይገኛሉ።

የውጭ ሀገር ዜጎቹም ከካሜሮን፣ ከሩዋንዳ፣ ከኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ከቶጎ እና ከኮንጎ መሆናቸው ተገልጿል።

ethiopian_gra_3.jpg

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለመተራቂ ሰልጣኞች ዲፕሎማቸውን የሰጡ ሲሆን፥ የእንኳን ደስ ያላችሁ እና እንኳን ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ በሰላም መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ethiopian_gra_2.jpg

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በአሁኑ ጊዜ 2 ሺህ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በተለያዩ ዘርፎች በማሰልጠን ላይ የሚገኝ ይገኛል።

የሰልጣኞቹን ቁጥር በአውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2025 4 ሺህ ለማድረስ እንደሚሰራ አየር መንገዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።