የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አራት ቦይንግ 777 ለመግዛት ተስማማ።

አየር መንገዱ የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ሲሆን፥ መቀመጫውን ቺካጎ ካደረገው የቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ቦይንግ 777 ኤከስን ለመግዛት እየተነጋገረ ይገኛል።

ስምምነት ከተደረሰባቸው አራት አውሮፕላኖች መካከል ሁለቱ፥ ባለፈው ሰኔ ወር በፓሪስ በተደረገው የአየር ትራንስፖርት አውደ ርዕይ ስምምነት የተደረገባቸው መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪ 777 ኤክስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት እየተደራደርን ነው ያሉት፥ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ናቸው።

አሁን ለመግዛት የተስማማናቸው አውሮፕላኖች አቅማችንን ለማሳደግ እንጅ፥ ሌሎች አውሮፕላኖችን ለመተካት አይደለም ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን በ2018/2019 እንደሚረከብ ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎት ላይ የሚገኙ ስድስት 777 ኤፍ የጭነት አውሮፕላኖች አሉት።

ምንጭ፦www.flightglobal.com