ቻይናዊው አዛውንት ለ36 ዓመታት ተራራ ቆፍረው የሚኖሩባትን መንደር የውሃ ተጠቃሚ አድርገዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ውስጥ በጉይዡ ግዛት የሚኖሩት የካኦዋንግባ መንደር ሊቀመንበር የሆኑት ሁናግ ዳፋ አኗኗራቸውን ለመቀየር ባደረባው ጉጉት ላለፉት 36 ዓመታት ለመንደራቸው ውሃ ለማስገኘት ተራራራ ሲቆፍሩ ነበር፡፡

ሰውየው ሶስት ተራራዎችን ቆፍረው ውሃ ካመነጩ በኋላ መንደሯ ከ10 ኪሎሜትር ርቀት ውሃ የምታገኝበትን የውሃ መስመር ዘርግተዋል፡፡

እኝህ ግለሰብ ይህን ተልዕኮ የጀመሩት የሚያስተዳድሯት መንደር ከእርሳቸው መኖሪያ ሁለት ተራሮችን ርቃ የምትገኝ በመሆኗ እና የውሃ አቅርቦትም ስላልነበራት የማህበረሰቡን አኗኗር ለማሻሻል በማለም እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ሁናግ ዳፋ ይህን እቅድ የጀመሩት በ1959 ሲሆን ለማሳካትም 36 ዓመታትን ጥይቋቸዋል፡፡

አሁን የሚያስተዳድሯት መንደር በማያቋርጥ የውሃ አቅርቦት ተጠቃሚ ሆናለች፡፡

በቻይናውያን አፈታሪክ ውስጥ አንድ ዩ ጎንግ የሚባ አፈታሪክ አለ፡፡

በዚህ አፈታሪክ ውስጥም ዩ ጎንግ የሚባሉ አባት ተራራን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ እዚህ ደርሷል፡፡

ታዲያ ቻይናውያኑ የካኦዋንግባ መንደር ነዋሪዎች ሊቀመንበራቸው ዳፋ የዩ ጎንግን ተረክ በተግባር ስላሳዩ አድናቆት እና ምርቃታቸው ከልክ በላይ ሆኗል፡፡

china_mountain_2.jpg

የመንደሯ ሰዎች ተራራ የመቆፈር ስራው ከተጀመረ ጀምሮ ለ10 ዓመታት ያህል 100 ሜትር የውሃ ማስተላለፊያ ቦይ ብቻ ነበር የሰሩት፡፡

ፋሮ ሲጀመር በፍርሃት እና በተስፋ መቁረጥ አንሳተፍም ያሉ የመንደሯ ነዋሪዎችም ነበሩ፡፡

china_mountain_3.jpg

የተራራ ቁፋሮው ሲጀመር እድሜያቸው 23 ዓመት የነበሩት የእና አሁን 80 ዎቹ በ80ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ሁናግ፥ በጣም አስቸጋሪውን ተራራን ቆራርጦ ውሃን ለመንደሯ የማድረስ እቅድ በፈረንጆች 1995 በማህበረሰቡ ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ እንዲጠናቀቅ አድርገዋል፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን እርሳቸው ሁሌም በስራ እንደተጠመዱ ናቸው፡፡

በመጨረሻም 7 ሺህ 200 ሜትር ርዝመት ለው ዋና የውሃ መስመር እና 2 ሺህ 200 ማከፋፈያ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የውሃ አቅርቦትን ለመንደሯ ማድረስ ጀምረዋል፡፡

china_mountain_4.jpg

አሁን ከተራራ ተጠልፎ የመጣው ውሃ 1 ሺህ 200 ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረጉም ተነግሯል፡፡

አዛውንቱ ሁናግ ዳፋ በ80ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ቢገኙም ለመንደሬ ሰዎች የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና የመንገድ መሰረተ ልማቶች እንደዲሟሉ አጥብቄ እፈልግ ነበር ብለዋል፡፡

ውሃ የሚያባክን የማህበረሰብ አባል ካለም ይቀጣል፡፡

ምንጭ፡-ኦዲቲ ሲንትራል