በሩሲያ የምትገኘው አትክልትና ፍራፍሬ ብቻ የሚመገቡ ሰዎች የሚኖሩባት ቬዳ መንደር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገረ ሩሲያ በምትገኘው የቬዳ መንደር ከአትክልት እና ፍራፍሬ ተመጋቢዎች በስተቀር ሌላ ሰው እንዲኖር አይፈቀድለትም።

በዚያች መንደር ስጋ መመገብ ባይችልም ለመብላት የሚፈቅድ ሰው ካለ በደንቡ መሰረት ከሰፈሩ ይሰናበታል።

በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ የቬዳ መንደር የሚል የቤት መርሃ ግብር በመገንባት ላይ ነው።

ይህ የቤት መርሃ ግብረ ጤና ሀይወት የሚኖር ማህበረሰብን ለመገንባት ፍላጎት ያላቸው እና አትክልት እና ፍራፍሬ ብቻ የሚመገቡ ሰዎች እንዲኖሩበት የታለመ ነው።

በቬዳ መንደር ቤት ተከራይቶም ሆነ ገዝቶ ለመኖር የሚፈልግ ሰው በቅድሚያ አትክልት እና ፍራፍሬ ብቻ የሚመገብ መሆን አለበት።

የሽያጭ ወኪሎች ገዥዎችን አግኝተው በሚጠይቋቸው ጥያቄ መሰረት፥ አትክልት ተመጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ካላቀረቡ የቤት ግዥ ወይም ኪራይ ውል ማመልከቻቸው ውድቅ ይሆናል።

በመስፈርቱ ቤት ለማግኘት ከስጋ የፀዳ ምግብ መመገብ ብቻ ሳይሆን፣ በመኖሪያ መንደሩ ውስጥ ምንም ዓይነት ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል መጠጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

የመኖሪያ መንደሩ የቤት ኪራይ እና የሽያጭ መመሪያ ዋና ዓላማው ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር መሆኑን የቬዳ መንደር ስራ አስከያጅ ማያ ፖድሊፕስካያ ተናግረዋል።

የቬዳ መንደር ነዋሪዎቿ በኤሌክትሪክ ሃይል፣ በውሃ፣ በፅዳት አስተዳደር እና በምግብ ዝግጅት ራሳቸውን የቻሉ እና ዘላቂ ህይወት እንዲኖራቸው ዓልማ ተነስታለች።

በመንደሯ ውስጥ የዮጋ ስፖርት ማዕከል፣ የጽዳት እና ውበት መጠበቂያ ቤቶች፣ የየዕለት የጤና ክትትል ማድረጊያ ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምግብ ቤቶችን ያካተተቱ ተቋማት እየተሰሩ ነው።

በመንደሩ ውስጥ አሁን ለመገንባት ከታቀዱት ባለብዙ ወለለል 7 ህንፃዎች መካከል ሁለቱ ተጠናቀዋል።

ቀሪዎቹን ደግሞ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት(2018) መጀመሪያ ለማጠናቅቅ እየተሰራ ነው ተብሏል።

አንዱ ህንፃ እስከ 210 ቤተሰቦችን ያስተናግዳል።

የቬዳ መንደር በሩሲያ የመጀመሪያዋ የአትክልት ተመጋቢዎች መኖሪያ ብትሆንም፥ በዓለም ላይ ተመሳሳይ መንደሮች ይገኛሉ።

በህንድ ቼናይ አካባቢ ተመሳሳይ መንደር በፈረንጆቹ 2012 መመስረቱ ይታወቃል።

 

 

 

ምንጭ፦ኦዲቲ ሴንትራል