በአንድ ወር ውስጥ ባለ 5 ሺህ፣ 500ና 5 ሚሊየን ዶላር ሎተሪ ያሸነፉት አሜሪካዊት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ነዋሪ በአንድ ወር ውስጥ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ጃክፖት ድረስ የሎተሪ እጣዎችን ማሸነፋቸው ተነግሯል።

ግለሰቧ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባለ 500፣ ባለ 5 ሺህ እና ባለ 5 ሚሊየን የሎተሪ እጣ እድለኛ መሆናቸውም ተነግሯል።

ብሬንዳ ጄንትሪ የተባሉት አሜሪካዊት ከሳምንታት በፊት ነበር በቨርጂኒያ ከተማ ውስጥ የሚሸጥ በሚፋቅ ፈጣን ሎተሪ 5 ሺህ ዶላር ማሸነፍ የቻሉት።

ባለ 5 ሺህ ዳለር ሎተሪያቸውን ሽልማት በተቀበሉ በቀናት ልዩነት ውስጥም በፋቁት ሌላ ሎተሪ የ500 ዶላር አሸናፊ መሆናቸውን ይናገራሉ።

ደስታቸውን አጣጥመው ያልጨረሱት ብሬንዳ ጄንትሪ፥ ሶስተኛ ላይ የደረሳቸው የሎተሪ እጣ ግን እጅግ በጣም አስደሳች ሆኖ ነበር ያገኙት።

ብሬንዳ ጄንትሪ ከአንድ የምግብ መሸጫ በቆረጡት የሎተሪ ትኬትም የ5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አሸናፊ መሆን ችለዋል።

አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሶስት ሎተሪ እድለኛ የሆኑት ብሬንዳ ጄንትሪ፥ ግብር የተቆረጠለት 2 ሚሊየን 808 ሺህ 989 የአሜሪካ ዶላር ተቀብለዋል።

“አሁን ያለኝን ኑሮ መቀየር አልፈልግም” ያሉት ብሬንዳ፥ አዲስ ባገኙት ገንዘብ የሚሰሩትን ለመወሰን መቸገራቸውንም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd