የካሊፎርኒያው ሰው በቦስተን ማራቶን ጀርባን ሰጥቶ ወደ ኋላ በመሮጥ አዲስ ሪኮርድ ለማስመዝገብ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የካሊፎርኒያ ነዋሪው የሆነው ሯጭ በቦስተን ማራቶን ጀርባን ሰጥቶ ወደ ኋላ በመሮጥ አዲስ ሪኮርድ በመያዝ ስሙን በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ለማስፈር በስልጠና ራሱን እያዘጋጀ ነው።

ሎረን ዚተመርስኪ የተባለ ግለሰብ የሩጫ ልምድ ያለው ሲሆን፥ በቦስተን በሚካሄደው ማራቶን 42 ኪሎ ሜትር ጀርባውን ሰጥቶ ሙሉ በሙሉ ወደ ኋላ በመሮጥ ከዚህ በፊት ተይዞ የነበረው ሪከርድ ለማሻሻል ማቀዱን አስታውቋል።

ይህም በዚህ የማራቶን ሩጫ የሚያገኘው ገንዘብ ለበጎ አድራጊዎች ለማበርከት ማሰቡን ነው የተናገረው።

ግለሰቡ ውድድሩን ከ3 ሰዓት 43 ደቂቃ እና 39 ሴኮንድ ባነሰ ጊዜ በመጨረስ አዲስ ሪኮርድ ለማስመዝገብ አላማ ማድረጉን ገልጿል።

ወደ ኋላ መሮጥ በእግሮቹ ላይ ብዙ ስቃይ ማስከተሉ የተናገረው ዚተመርስኪ፥ ነገር ግን ስቃዩ የበጎ ተግባር የሚፈፅመው እና በውድድሩ የሚያገኘውን ገቢ የሚለግስለት

ተቋም የሚንከባከባቸው የሚጥል በሽታ ያለባቸው ታካሚዎች ከሚገጥማቸው ትግል ጋር አይነፃፀርም ነው ያለው።

ለዚህም “ወደ ኋላ ስሮጥ የሚሰማኝ ሕመም ጊዜያዊ ነው፤ በሚጥል በሽታ ስቃይ ያሉ ሰዎች ግን በየቀኑ በችግሮች ውስጥ ይኖራሉ” ሲል ገልጿል።

ምንጭ፦www.upi.com