10 ቀይና 8 ቢጫ ካርዶች የተመዘዙበት የእግር ኳስ ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 10 ቀይ እና ስምንት ቢጫ ካርዶች በአንድ ጊዜ የታዩባቸው የቪቶሪያና ባሂያ እግር ኳስ ጨዋታ በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገርያ ሆኗል።

ቪቶሪያ እና ባሂያ ሁለቱም ክለቦች በብራዚል ባሂያ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

የብራዚል ተጫዋቾች በእግር ኳስ ክህሎታቸው እጅጉን የታወቁ ቢሆኑም፥ ሰሞኑን በባሂያ ግዛት በቪቶሪያና ባሂያ ክለቦች መካከል በተካሄደው የሻምፒዮን ጨዋታ የታየው የተጫዋቾች ባህሪ ከዚህ የተለየ እንደነበር ተነግሯል።

ለዚህም ሁለቱም ክለቦች ካደረጉት የመጀርያው ግማሽ ጨዋታ በኋላ ከእግር ኳስ ስነ ምግባር ውጭ የሆኑ ተግባራት መታየታቸው ነው የተጠቆመው።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ባሂያ በ50ኛው ደቂቃ ላይ ባገኘው የቅጣት ምት መሰረት ቪኒሲዮስ የተባለ ተጫዋች ለክለቡ የመጀመርያ ጎል ያስቆጥሯል።

በዚህ ምክንያት ቪኒሲዮስ በተቃራኒው ቡድን ደጋፊዎች ፊት በመጨፈሩ ነበር በሁለቱ ክለብ ተጫዋቾች መካከል ጭቅጭቁ የተነሳው።

በዚህም መሰረት ሁሉም ተጫዋቾች ቦክስ መሰነዛዘር የጀመሩ ሲሆን፥ ጨዋታው ለ16 ደቂቃዎች ተቋርጧል።

በተጨማሪም የመሃል ዳኛው ጥፋት ፈፅመዋል ላላቸው ስምንት ተጫዋቾች ቀይ ካርድ አሳይቷል።

_100083268_flashscore.jpg

ይህም ቪኒሲዮስ ጨምሮ ሶስት ቀይ ካርዶች ለቫቶሪያ ተጫዋቾች እና አምስት ለባሂያ ተጫዋቾች በመስጠት ከሜዳ አስወጥቷቸዋል።

በዚህም ጨዋታው የቀጠለ ሲሆን፥ ነገር ግን ከ11 ደቂቃዎች በኋላ ቪቶርያ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ አጥቷል።

ስለሆነም ጨዋታው እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን፥ ጨዋታው በባሂያ 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ