የቻይና ኤር በረራን በስክብሪቶ ያስተጓጎለው ግለሰብ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 8፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበረራው ላይ የነበረ ግለሰብ እስክብሪቶውን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም የበረራ አስተናገጇን በማገቱ ባሳለፍነው እሁድ የቻይና ኤር በረራውን እንዳቋረጠ የቻይና ባለስልጣን መግለጫ ሰጥቷል ተብሏል።

በዚሁ ጉዳይ በበረራ ቁጥር ሲኤ 1350 ከቻንጋሻ ወደ ቤጂንግ ያመራ የነበረው ቻይና ኤር በሀናን ግዛት እንዲያርፍ መገደዱም ነው የተገለጸው።

 በክስተቱ በበረራ ቡድኑም ላይ ይሁን በደንበኞች ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ተገልጿል።

ግለሰቡ ከበረራ አስተናጋጆች በአንዷ አንገት ላይ እስክብሪተውን እንደጦር መሳሪያ አድርጎ ይዞ ፎቶውን በቻይና ሶሻል ሚዲያ ሰዎች ሲቀባበሉት እንደነበረም በዘገባው ተገልጿል።

የሀናን የጸጥታ ቢሮ በመግለጫው እንዳሳወቀው በበረራው ላይ የነበረ ግለለሰብ ድንገተኛ የአዕምሮ ህመም ገጥሞታል።

በዚሁ ተግባር የተጠረጠረው የ41 ዓምቱ ዡ ወደ ወህኒ የወረደ ሲሆን፦ የአዕምሮ ጤና መታወክ ታሪክ ያለው እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ሰውዬው ቀደም ሲል የአዕምሮ በሽታ የነበረበት መሆኑ ከተረጋገጠም በወንጀለኝነት እንደማይፈረጅ የሀገሪቱ የህግ ባለሞያዎች እንደተናገሩ ቢቢሲ ዘግቧል።

 

 

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ


የተተረጎመና የተጫነው ፦ እንቻለው ታደሰ