ከ47 ዓመት በኋላ የእጅ ቀለበቷን ያገኘችው ግለሰብ

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት የጠፋው ቀለበት ከ47 ዓመት በኋላ ለባለቤቷ እንደተመለሰሰ ተሰምቷል።

ይህ ቀለበት የሚቺጋን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የማስፋፊያ ግንባታ በሚከናወንበት ወቅት ነው የተገኘው።

ዱጎ ሉድዊክ የተሰኘ ግለሰብ በተማሪዎች የእቃ ማስቀመጫ ሳጥን (ሎከር) ላይ በጊዜው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሚያጠናቁቁበት ወቅት ለማስታወሻነት የሚያጠልቁትን ቀለበት እንደገኘው ተነግሯል።

ይህ ቀለበት በፈረንጆች 1971 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲጠቀሙበት የነበረ ቀለበት እንደሆነ ተጠቁሟል።

በዚህም ቀለበቱን ያገኘው ግለሰብ ለትምህትርት ቤቱ አስተዳደር በማስረከቡ ቀለበቱ ላይ በሰፈረው ስም ባለቤቱን የመለየት ስራ ተከናውኗል።

በመሆኑም ለ47 ዓመት ጠፍቶ የነበረው ይህ ቀለበት አንጄሊታ ኦሊቫሩስ ውይንም በአሁኑ ወቅት አንጄሊታ ኮሎዝየስስኪ የተባለች ግለሰብ ንብረት ሆኖ ተገኝቷል።

ይህን ቀለበት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት እንደገዛችውና ለመመሪቂያ እንዲሆናት ማስቀመጧን አስታውሳለች።

ቀለበቱን እቃ ማስቀመጫ ሳጥን (ሎከር) ውስጥ ማስቀቀመጧን ቀለበቱ ስለጠፋበት አጋጣሚ ታስታውሳለች በዚህም ትምህርት ሲጠናቀቅ ቀለበቱን ወዳስቀመጠችበት ብታመራም በቦታው እንዳላገኘችውና ተስርቋል ብላ አስባ እንደነበር ተናግራለች።

የጠፋባትን ቀለበት ከ47 ዓመት በኋላ በማግኘቷ ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች።

ምንጭ፦ upi