በሰውነታችን ውስጥ በሽታ ሊከሰት እንደሚችል ምልክት የሚያሳዩ ንቅሳቶች

አዲስ አበባ ሚያዚያ፣ 12፣ 210(ኤፍ.ቢ.ሲ) ቀደም ሲል ሰዎቹ ለጌጥና ታማኝነትን ለመግለጽ የሰዎችን ስምና ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ይዘት ያላቸው ንቅሳቶችን በሰውነታቸው ላይ መነቀስ የተለመደ ነበር።

ተመራማሪዎች በአይጦች ላይ ባደረጉት ምርምር ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ በሽታ ሊከሰት እንደሆነ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚሰጡ ዘመናዊ ንቅሳቶች እንዳገኙ ተገልጿል።

 አዲሶቹ ንቅሳቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በሰውነት ውስጥ ሲቀመጡ ከሌላው የሰውነታችን ክፍል በተለየ ሁኔታ የማይታዩ ሲሆን፥ በሰውነት ውስጥ የካልሼም ንጥረ ነገር ሲጨምምር መታየት እንደሚጀምሩም ነው የተገለጸው።

በሳይንሳዊዩ የንቅሳት ዘዴ በሰውነት ውስጥ የካልሼም መጠን ለመለካት የሚችሉ ‘‘ሴንሰሮች’’ የተገጠሙላቸው ሴሎችን እንዲቀመጡ እንደሚደረግም በዘገባው ተገልጿል።

የአንጀት፣ የሳንባና ‘‘ፕሮስቴት’’ ካንስር ሲከሰቱ በሰውንት ውስጥ የካልሼም መጠን የሚዋዥቅ ሲሆን፥ ንቅንቅሳቶቹ በሽታዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሳያድጉ በስውነታችን ውስጥ የካልሼም መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ምልክት የሚሰጡ ሆነው እንደተዘጋጁ ነው ጥናቱ የሚያስረዳው።

በዚህም የሳይንሳዊ ንቅሳቶቹ በሰውነታችን ውስጥ የካንሰር በሽታ ሊከሰት ስለመሆኑ ‘‘ሜላኒን’’ የተባለ ንጥረ ነገር በማመንጨት በቆዳችን ላይ ጥቁር ምልክት እንደሚያሰዩም ታውቋል።

ሳይንሳዊ ግኝቱ በይዘቱ በአዲስ ስልት በሽታዎችን ለመለየት የሚያስችልና የሰዎችን ትኩረት የሳበ እንደሆነ በኒው ዮርክ የካንስር ማዕክል የካንስር ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ጃኒስ ዱቸር ተናግረዋል።

ነገር ግን የኩላሊት ካንሰርን የመሰሉ የካንሰር አይነቶች በሽታው ከተከሰተ በኋላ የካልሼም ንጥረ ነገር ሊጨምር እንደሚችልና ሁሌም በሰውነት ውስጥ የካልሼም ንጥረ ነገረ መጨመር የካንሰር ህመም መከሰትን ሊገልጽ እንደማይችል ተጠቅሷል።

ጥናቱ ባይጦች ላይ የተሰራ ሲሆን፥ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በሰዎች ላይ ውጤታማነቱ እንደሚረጋገጥም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ upi.com

 

የተተረጎመና የተጫነው፦ እንቻለው ታደሰ