የሜክሲኮ ፖሊሶች በሽጉጥ ምትክ ወንጭፍ እንዲታጠቁ መደረጉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሜክሲኮዋ አልቫራዶ ከተማ የሚገኙ ፖሊሶች በሽጉጥ ምትክ የድንጋይ መወርወሪያ ወንጭፍ እንዲታጠቁ መደረጉ ተሰምቷል።

ፖሊሶቹ ሽጉት አስቀምጠው ወንጭፍ እንዲታጠቁ የተደረገበት ምክንያት ደግሞ የቀረበላቸውን ራስን የመቆጣጠር ፈተና ማለፍ ባለመቻላቸው እንደሆነም ተነግሯል።

ለ130 የአልቫራዶ ከተማ ፖሊሶች ራስን የመቆጣጠር ፈተና ተሰጥቶ ከእነዚህ ውስጥ 30 ፖሊሶች ብቻ ፈተናውን ያለፉ ሲሆን፥ 100 ፖሊሶች ደግሞ መውደቃቸው ተነግሯል።

ፈተናውን ተከትሎም የጦር መሳሪያ መታጠቅ ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን መቆጣጠር የሚችሉ ብቻ ናቸው በመበባሉ 30 ፖሊሶችቨ ብቻ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁ ተደርጓል።

ቀሪዎቹ 100 የአልቫራዶ ከተማ ፖሊሶች ራሳችውን መቆጣጠር አይችሉም በሚል የያዙት የጦር መሳሪያ ተቀምቶ በምትኩ የድንጋይ መወርወሪያ ወንጭፍ እንዲጠቀሙ ተደርጓል።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com