ስፖርት (1193)

አዲሰ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2017ቱ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲየም ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተቀላቅሏል፡፡ትናንት የተጀመረው ጨዋታ በሀዋሳ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሜዳው ውሀ ቋጥሮ ማጫወት ባለመቻሉ በ55ኛው ደቂቃ በዳኛው ውሳኔ መቋረጡ ይታወሳል።

የጨዋታው ኮሚሽነር ጉዳዩን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካሳወቁ በኋላም ቀሪ 35 ደቂቃዎች ዛሬ ረፋድ 4 ሰአት ላይ እንዲደረጉ ሆኗል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በትናንትናው እለት ሳላሃዲን ሰይድ፣ አዳነ ግርማ እና አስቻለው ታመነ ባስቆጠሯቸው ግቦች ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ያረጋገጠው።
ዛሬ የጨዋታው ቀሪ ደቂቃዎች ሲደረጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ እንቅስቃሴን ቢያደርግም ተጨማሪ ግብ ሳይስቆጥር ቀርቷል። በመከላከሉ የተሻሉ ሆነው የቀረቡት ኮት ዲ ኦሮች በሳላሃዲን ሰይድ እና በሀይሉ አሰፋ እንዲሁም ፍሬዘር ካሳ አማካኝነት የተፈጠሩ ግልፅ የግብ አጋጣሚዎችን አምክነዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታውን በድምር ውጤት 5-0 በሆነ ውጤት ማሸነፋን ተከትሎ በቀጣዩ ዙር ከኮንጎ ብራዛቪሉ ኤሲ ሊዮፓርድስ ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡
በኮት ዲኦር ላይ 3 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ሳላሃዲን ሰይድ ናይጄሪያዊው ጆን ጀርማያህ እና ሊብያዊው ሞአያድ አላፊን በመብለጥ የቻምፒየንስ ሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ሰንጠረዥ በመምራት ላይ እንደሚገኝም ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዳማ ከተማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ዋና አሰልጣኝ ተደርገው ተመርጠዋል።

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ተደርገዋል።

አዲሰ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ምሽት በተደረጉ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ባየር ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቷቸዋል።