46ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) 46ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።

በውድድሩ ሁሉም ክልሎች እና 30 ክለቦች ተሳታፊ ሲሆኑ፥ 1 ሺህ 265 አትሌቶችም ይካፈላሉ ተብሏል፡፡

ዛሬ የስሉስ ዝላይ እና የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ፍጻሜ ተካሂዷል።

በወንዶች የስሉስ ዝላይ የመከላከያው አዲር ኑር 15 ሜትር ከ79 ሴንቲሜትር በመዝለል አሸናፊ ሆኗል።

ብርሃኑ ሞዲሳ እና ጌቱ ደቀባ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ደግሞ ዙርጋ ኡስማን ከሲዳማ ቡና፣ መሰረት ከበደ ከመከላከያ እንዲሁም ሰላማዊት ማሬ ከደቡብ ፖሊስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር በሴቶች ዲራ ዲዳ ከኦሮሚያ አሸናፊ መሆን ችላለች።

እታገኝ ወልዱ ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ስትሆን፥ ገበያነሽ አያሌው ከመከላከያ ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።፡

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ደግሞ፥ የሲዳማ ቡናው ሃይለአምላክ 28 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ በመግባት በበላይነት አጠናቆታል።

ሙክታር እድሪስ እና አባዲ አዲስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡

ውድድሩ ነገም በተለያዩ ውድድሮች ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል፥ በመጭው እሁድም ፍጻሜውን ያገኛል።