ገንዘቤ በ5000 ሜትር የማጣሪያ ውድድር አትሳተፍም

አዲስ አበባ ነሃሴ 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ዛሬ ምሽት 2 ስአት ከ30 ላይ በሚካሄደው የ5000 ሜትር ማጣሪያ ውድድር እንደማትሳተፍ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ገንዘቤ ባጋጠማት የጀርባ ህመም ምክንያት ነው በማጣሪያው የማትካፈለው ብሏል ፌዴሬሽኑ።

በምሽቱ የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ የ10 ሺህ ሜትር ሻምፒዮናዋ አትሌት አልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ለተሰንበት ግደይ ኢትዮጵያን ይወክላሉ።

ሰባተኛ ቀኑን በያዘው የ16ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ምሽት 3 ስአት ከ25 የ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ የሚደረግ ሲሆን ሀብታም አለሙ፣ ማህሌት ሙሉጌታ እና ኮሬ ቶላ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።

ምሽት 4 ስአት ከ25 ላይ ደግሞ የ1500 ወንዶች ማጣሪያ ይካሄዳል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በአንድ የወርቅና በሁለት የብር ሜዳልያዎች ከዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ከአፍሪካ ደግሞ ከኬንያና ደቡብ አፍሪካ ቀጥላ 3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

medal.png