በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ16ኛው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ።

በውድድሩ ኢንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ሁለተኛ ሲወጣ፥ ዮሚፍ ቀጄልቻ አራኛ እና ሰለሞን ባረጋ አምስተኛ ወጥቷል።

በለንደን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው 16ኛው የዓለም አቅሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጠናቀቃል።

እስካሁን በተደረገው ውድድርም ኢትዮጵያ የዛሬውን ጨምሮ ሁለት የወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎቸን ማግኘት ችላለች።