በፕሪሚየር ሊጉ ሃዋሳ ከተማ ሲያሸንፍ አዳማና ደደቢት አቻ ተለያይተዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች ትናንትና ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል።

ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ ወላይታ ዲቻን አስተናግዶ፥ ወላይታ ዲቻዎች ጨዋታውን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል።

ዛሬ ደግሞ አምስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከደደቢት ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ይርጋለም ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ከተማ ሳይሸናነፉ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ወልዲያ ከተማን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ ደግሞ በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።

በሃዋሳ ከተማ 4 ለ 1 አሸናፊነት በተጠናቀቀው ጨዋታ ዳዊት ፍቃዱ ሶስት ጎል በማስቆጠር ሃት- ትሪክ ሰርቷል።

በትግራይ ደርቢ ደግሞ መቐለ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ ላይ ተገናኝተው፥ ጨዋታቸውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር ተገናኝተው ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ታህሳስ 18 ይገናኛሉ።

 ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ለጥር 10 ተራዝሟል ።