ኢትዮጵያ ከ2018ቱ የቻን ውድድር ውጭ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከ2018ቱ የአፍሪካ ሃገራት ሻምፒዮና (ቻን) ውድድር ውጭ ሆነች።

ዛሬ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ኪጋሊ ላይ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታውን ያለጎል በአቻ ውጤት አጠናቋል።

በኪጋሊ ብሔራዊ ስታዲየም ጎል አልባ ጨዋታ ያደረገው ቡድኑ በድምር ውጤት ተሸናፊ ሆኗል።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎም ኢትዮጵያ ከጥሩ ውድድር ውጭ ስትሆን ሩዋንዳ ደግሞ ተሳታፊ መሆኗን አረጋግጣለች።

በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ሩዋንዳ 3 ለ 2 ማሸነፏ ይታወሳል።