በቻምፒየንስ ሊጉ ታላላቆቹ ቡድኖች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል።

ከምድብ 1 እስከ 4 በሚገኙ ቡድኖች መካከል በተደረጉ ጨዋታዎች 8 ቡድኖች ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

በምድብ 1 የእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ሲ ኤስ ኬ ሞስኮን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።

ወደ ፖርቹጋል ያቀናው ባዜል ደግሞ ቤኔፊካን 2 ለ 0 አሸንፎ ተመልሷል።

በምድብ 2 ለበላይነት በተደረገ ጨዋታ ባየርን ሙኒክ ፒ ኤስ ጂን 3 ለ 1 አሸንፎታል።

በሌላው የምድብ ጨዋታ ሴልቲክ በሜዳው በአንደርሌክት 1 ለ 0 ተሸንፏል።

በምድብ 3 ደግሞ ቼልሲ ከአትሌቲኮ ማድሪድ አንድ አቻ ሲለያይ የጣሊያኑ ሮማ የአዘርባጃኑን ቃራባግን 1 ለ 0 አሸንፎታል።

በምድብ 4 ባርሴሎና ስፖርቲንግን እንዲሁም ጁቬንቱስ ከሜዳው ውጭ ኦሊምፒያኮስን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ከምድብ 1 ማንቼስተር ዩናይትድና ባዜል፣ ከምድብ 2 ፒ ኤስ ጂና ባየርን ሙኒክ፣ ከምድብ 3 ሮማና ቼልሲ እንዲሁም ከምድብ 4 ባርሴሎናና ጁቬንቱስ 16ቱን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

ከምድብ 5 እስከ 8 ያሉ ቡድኖች ደግሞ ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።