የኢትዮጵያ ቡናና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ አንድ ጨዋታ አስተናግዷል።

ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን እና ሀዋሳ ከተማን አገናኝቷል።

በደጋፊዎች ታጅቦ የተካሄደው ጨዋታ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በዚህም መስዑድ መሐመድ በ86ኛ ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናን መሪ ማድረግ ቢችልም፥ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን በ88ኛ ደቂቃ ላይ ሀዋሳ ከተማን አቻ አድርጎ ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቋል።

በአጠቃላይ ፕሪሚየር ሊጉን ደደቢት በ28 ነጥብ ሲመራ፥ መቐለ ከተማ በ25 ነጥብ ይከተላል።

አዳማ ከተማ በ23 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ሆኖ ሲቀመጥ፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከተማ በተመሳሳይ 22 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 4ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ዛሬ ጨዋታውን ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና 20 ነጥብ በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፥ ሀዋሳ ከተማ በ15 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።