በፕሪምየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ መከላከያ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዛሬው እለት አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አስተናግዷል።

የፕሪምየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ መከላከያን ከመቐለ ከተማ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ያገናኘ ጨዋታ ነበር።

ዛሬ የተደረገው ጨዋታም በመከላከያ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለመከላከያ የማሸነፊያ ግብ በ60ኛው ደቂቃ ምንይላሉ ወንድሙ አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በትናንትናው እለትም አንድ ጨዋታ ያስተናገደ ሲሆን፥ ጨዋታምው ኢትዮጵያ ቡናን እና ሀዋሳ ከተማ መካከል ነበር የተደረገው።

ኢትዮጵያ ቡናን እና ሀዋሳ ከተማ መካከል የተካሄደው ጨወዋታም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።