ሮናልዲኒሆ ጉቾ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ይዞ አዲስ አበባ ይገኛል

አዲስ አበባ ሚያዚያ 6፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብራዚሊያዊ ኮኮብ የእግ ኳስ ተዋጫች ሮናልዲኒሆ ጉቾ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ይዞ አዲስ አበባ ይገኛል።

ሮናልዲኒሆ ጉቾ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን በመያዝ በዛሬው ዕለት ነው አዲስ አበባ የገባው፡፡

በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላም የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክር ወርቅነህ ገበየሁ የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ሮናልዶ ዲ አሲስ ሞሬራን (ሮናልዲኒሆ ጎቾ) ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ሮናልዲኒሆን ሲቀበሉ የሰው ልጅ መገኛ ወደ ሆነችዉ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ብለውታል።

worke_1.jpg

የስፖርት ዲፕሎማሲው የዘመናዊ ዲፕሎማሲ አካል መሆኑን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፥ ስፖርት ዘር እና ሀይማኖትን ሳይለይ ለሰዎች አንድነት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ስፖርት በተለይ የእግር ኳስ ዓለምን እንደ አንድ አድርጎታል ያሉት ዶክተር ወርቅነህ የሮናልዲኒሆ የግል አድናቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የጠንካራ አትሌቶች አገር የመሆኗን ያህል ብራዚልም የእግር ኳስ ታዋቂ ተጫዋቾች አገር ናት ብለዋል።

ዶክተር ወርቅነህ እንደገለፁት፥ ሮናልዲኒሆን ያበቀለችሁ ብራዚል እና ኢትዮጵያ ብዙ ተመሳሳይነት አላቸው፤ ኢትዮጵያ እንደ አበበ ቢቂላ ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣ ሀይሌ ገብረስለሴ፣ ቀነኒሳ በቀለ ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ የዲባባ ቤተሰቦች እና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችን ያፈራች አገር ብለዋል።

በተመሳሳይም ብራዚል የእና ፔሌ፣ ስቆራትስ ፣ዱንጋ ፣ቤቤቶ፣ ሮማሪዮ ሮናልዶ፣ ኔማር የመሰሉ የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ልጆች እናት ናት ከእነርሱ አንዱ ጎቾ ነው።

worke_2.jpg

ሮናልዲኒሆ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቅሶ፤ ስለ ሀገሪቷ የበለጠ ለማወቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲታዩ ጠንክረው መስራት አለባቸው ማለቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሮናልዲኒሆ ጉቾ በቆይታው እሁድ ጥዋት አዲስ አበባ ስታድየም ከተመልካቾች ጋር እንደሚገናኝ የሚገናኝ ሲሆን፥ ከ20 ዓመት በታች ወጣቶችን ጨዋታ እንደሚመለከትም ተነግሯል።