ሴካፋ በኢትዮጵያ ላይ የ5 ሺህ ዶላር የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 8 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴካፋ በኢትዮጵያ ላይ የ5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ።

ቅጣቱ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ትናንት በሴካፋ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ከሶማሊያ አቻው ጋር ባደረገው የማጣሪያ ጨዋታ ያልተገቡ ተጫዋቾችን ተጠቅሟል በሚል የተላለፈ ነው ተብሏል።

ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪም የትናንቱ ጨዋታ ውጤት ተሰርዞ ሶማሊያ በፎርፌ እንድታሸንፍም ወስኗል።

በትናንት ጨዋታ ቡድኑ ሶማሊያን 3 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ሶማሊያ በጨዋታው ኢትዮጵያ ሶስት የእድሜ ተገቢነትን የማያሟሉ ተጫዋቾችን ተጠቅማለች በሚል ለሴካፋ ቅሬታዋን አቅርባ ነበር።

ይህን ተከትሎም ሴካፋ ከላይ የተጠቀሰውን ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ይግባኝ ጠይቋል።

 

 


ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ