አብደላ ጎዳና በጃፓን ናጋኖ ማራቶንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2010 (ኤፍቢሲ) ኢትዮጵያዊው አብደላ ጎዳና በጃፓን በተደረገ የናጋኖ ማራቶን ውድድር አሸነፈ።

አብደላ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ሁለት ሰዓት ከ13 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ ፈጅቶባታል።

እንዲሁም በሴቶች በተደረገው በዚህ የማራቶን ውድድር ከ2001 በኋላ ጃፓናዊቷ አሳሚ ፉሩሴ አሸንፋለች።

ሁለቱም ውድድሩን ሲያሸንፉ የመጀመሪያቸው መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም ፖላንድ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር መስፍን አለሙ አንደኛ ወጥቷል።

መስፍን ግማሽ ማራቶኑን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ ወስዶበታል።

መስፍን የውድድሩን አብዛኛውን ርቀት በብቸኝነት እንደመራ የተገለጸ ሲሆን፥ ኬኒያዊው ሂላሪ ማዮ በ24 ሰከንድ ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ወጥቷል፤ አማኑኤል ብርሃኑ ደግሞ በሶስተኝነት ውድድሩን አጠናቋል።