በዓለም ዋንጫው ስዊድን እና ቤልጂየም ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛ ቀኑን የያዘው የዓለም ዋንጫ ዛሬ የምድብ ስድስት እና ሰባት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

ከቀትር በኋላ 9 ሰዓት ላይ በተደረገ የምድብ ስድስት ጨዋታ ስዊድን ደቡብ ኮሪያን አሸንፋለች።

በጨዋታው ስዊድኖች በ65ኛው ደቂቃ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት የቡድኑ አንበል ግራክቪስት አስቆጥሮ አሸናፊ አድርጓቸዋል።

በምድብ ሰባት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ጠንካራ ስብስ የያዘው የቤልጂየም ብሄራዊ ቡድን ፓናማን አሸንፏል።

ድሪዬስ መርተንስ አንድ እንዲሁም ሮሜሉ ሉካኩ ደግሞ ሁለት ጎሎችን ለቤልጂየም አስቆጥረዋል።