ዜናዎች (14260)

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸውን የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጃኮብ ሙንዴንዳ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘውዲቱ ሆስፒታል ከአንድ ዓመት በፊት ለአምስት የኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) መሳሪያዎች ግዥ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ቢያገኝም እስካሁን ግዥ አለመፈፀሙ ታካሚዎች ህክምናውን በቀላሉ እንዳናገኝ አድርጎናል የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ማስተካከያ መደረጉ መድሃኒቶችን ለማቅረብ ጨርታ ያሸነፉ የግል ድርጅቶች እና የመንግስት ተቋማትን በማወዛገብ ላይ ነው።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ኢራቅ ቱዝ ኩርማቱ ከተማ በመኪና ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊዎች የቦምብ ጥቃት በትንሹ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉን የህክምና መረጃዎች ገልፀዋል።