ግብጽ "የያዘችውን የሱዳን ይዞታ" በተመለከተ ካርቱም በትዕግስት ለመፍታት ጥረት እያደረገች መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የሱዳን ፕሬዚዳንት ሀገራቸው ከግብጽ ጋር የገባችበትን የይዞታ ወዝግብ በትእግስት ለመፍታት እንደሚጥሩ አስታወቁ።

ከቅርብ ወራት ወዲህ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ግብጽ የሱዳን ተቃዋሚ መሪዎችን እየረዳች መሆኗን መግለጻቸውን ተከትሎ የካይሮ እና ካርቱም ግንኙነትን የሚያሻክሩ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ናቸው።

ግብጽ በቀይ ባህር አካባቢ የሚገኝ አወዛጋቢውን የሱዳን ይዞታዬ ነው የምትለውን ቦታ በህገወጥ መንገድ መያዟ እየተነገረ ይገኛል።

ፕሬዚዳንት አልበሽር ይህንን አስመልክተው ለአልጀዚራ እንደተናገሩት፥ ግብጽ "በህገ ወጥ መንገድ ቀይ ባህር አቅራቢያ የሚገኘውን አካራካሪ የግዛታችን ይዞታ ይዛለች" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ግብጽ ሃሊብ ትሪያንግልን መያዟን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፥ ሱዳን የሁለቱን ሀገራት የረዥም ዘመን ግንኙነት ለማክበር ሲባል እስካሁን ዝምታ መምረጧን ከአልጀዚራ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ግብጽ የሱዳንን ግዛት በመውረር መያዟን የተናገሩት አልበሽር "አንድም ነገር አላደረግንም፤ ምንም የተሳሳተ ነገር አልተናገርንም" ነው ያሉት።

በዘንደሮው የአውሮፓውያን አዲስ አመት መጀመሪያ አካባቢ "ሃሊብ-ሻላቲን ትሪያንግል" የሱዳን መሆኑን በመጥቀስ ሀገራቸው የተወሰደባትን ግዛት ለማስመለስ ወደ ጦርነት እንደማትገባ እና ግዛቷን በድርድር እንደምታስመልስ ነበር የተናገሩት።

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ ኤልሲሲ በፕሬዚዳንት ከመመረጣቸው በፊት ሃሊብ-ሻላቲን ትሪያንግል የግብጽ ግዛት መሆኑን እና ሱዳን በዚህ ጉዳይ ከግብጽ ጋር ግጭት ውስጥ መግባት እንደሌለባት አሳስበው ነበር።

 

ምንጭ፦ http://www.egyptindependent.com

 

 

በእስክንድር ከበደ