የአሜሪካን የስላለ አውሮፕላን በሁለት የቻይና ጄቶች ቅኝቱን እንዳያደርግ ተገደደ

 አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ)የቻይና ሁለት ሱ-30 የጦር ጄቶች በምስራቅ ቻይና ባህር የአየር ክልል ውስጥ ቅኝት ሲያደርግ የነበረን ፥የአሜሪካ የስለላ አውሮፕላን በማጀብ ክትትል ማደረጋቸውን አሜሪካ አስታወቀች፡፡

ከሁለቱ ጄቶቹ አንደኛው በአሜሪካ ደብሊዩ ሲ-135 በተሰኘው ጄት ላይ በቅርበት ተገልብጦ ብረ እንደነበር  የአሜሪካ ወታደራዊ ቃለአቀባይ ለቢቢሰ ገልጸዋል፡፡

ጄቶቹ የአሜሪካኑን የቅኝት አውሮፕላን በቅርበት በመከታተል አውሮፕላኑ መብረር ከሚኖርበት ከፍታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጫማዎች ወደታች እንዲወርድ አስገድደውታል ተብሏል፡፡

ይህንንም “ያልተገባ ድርጊት“በሚመለከተው የዲፕሎማሲ እና ወታደራዊ መንገድ ቻይና እንድታውቀው መደረጉን ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት ፡፡

የአሜሪካ አየር ሃይል ንብረት የሆነው ይህ “ደብልዩ ሲ-135 “ የጦር አውሮፕላን በምሰራቅ ቻይና ባህር አየር ክልል በተደጋጋሚ ቅኝት በማድረግ ይታወቃል፡፡

የስለላ አውሮፕላኑ “የኑክሌር አነፍናፊ“ በመባል የሚጠራ ሲሆን፥በሰሜና ምስራቅ እስያ የአየር በረራ በማካሄድ የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ፕሮግራም ቅኝት የማደረግ አላማ እንዳለው የአሜሪካ ባለስልጣናት ይናገራሉ፡፡

ምንጭ ፦ቢቢሲ

 


በእስክንድር ከበደ